ዘፍጥረት 27:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እርሱም ቀረበ፤ ሳመውም፤ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፤ ባረከውም፤ እንዲህም አለ፥ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው፤ ይሥሐቅ የያዕቆብን ልብስ ካሸተተ በኋላ እንዲህ ብሎ መረቀው፤ “እነሆ፤ የልጄ ጠረን፣ እግዚአብሔር እንደ ባረከው፣ እንደ መስክ መዐዛ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ እርሱም ቀረበ፥ ሳመውም፥ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፥ ባረከውም፥ እንዲህም አለ፦ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው። ይስሐቅ የያዕቆብን ልብስ ባሸተተ ጊዜ እንዲህ ሲል መረቀው፥ “እነሆ የልጄ መልካም ሽታ፥ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እርሱም ቀረበ ሳመውም የልብሱንም ሽታ አሸተት ባረከውም እንዲህም አለ፦ የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፤ |
ርብቃም ከእርስዋ ዘንድ በቤት የነበረውን የታላቁን ልጅዋን የዔሳውን መልካሙን ልብስ አመጣች፤ ለታናሹ ልጅዋ ለያዕቆብም አለበሰችው፤
የእስራኤልም ዐይኖች ከሽምግልና የተነሣ ከብደው ነበር፤ ማየትም አይችልም ነበር፤ ወደ እርሱም አቀረባቸው፤ ሳማቸውም፤ አቀፋቸውም።
ያዕቆብም ባረካቸው፤ እንዲህም አለ፥ “አባቶች አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ ደስ ያሰኙት እርሱ እግዚአብሔር፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፥
በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ፥ መዓዛቸውንም ሰጡ፤ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፤ መልካምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ። በዐለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ወዳለው ጥላ ነዪ።
ምድርም በእርስዋ የሚወርደውን ዝናም ከጠጣች፥ ያንጊዜ ስለ እርሱ ያረሱላትን መላካም ቡቃያ ታበቅላለች፤ ከእግዚአብሔር ዘንድም በረከትን ታገኛለች።