Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 27:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ወደ እርሱም ቀረበ፥ ሳመውም፥ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፥ ባረከውም፥ እንዲህም አለ፦ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው፤ ይሥሐቅ የያዕቆብን ልብስ ካሸተተ በኋላ እንዲህ ብሎ መረቀው፤ “እነሆ፤ የልጄ ጠረን፣ እግዚአብሔር እንደ ባረከው፣ እንደ መስክ መዐዛ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው። ይስሐቅ የያዕቆብን ልብስ ባሸተተ ጊዜ እንዲህ ሲል መረቀው፥ “እነሆ የልጄ መልካም ሽታ፥ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ወደ እር​ሱም ቀረበ፤ ሳመ​ውም፤ የል​ብ​ሱ​ንም ሽታ አሸ​ተተ፤ ባረ​ከ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የልጄ ሽታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ባረ​ከው የእ​ርሻ ሽታ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ወደ እርሱም ቀረበ ሳመውም የልብሱንም ሽታ አሸተት ባረከውም እንዲህም አለ፦ የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 27:27
14 Referencias Cruzadas  

ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፥ ለሚያርሱአትም ደግሞ የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል፥ ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፤


ምድርን ጐበኘሃት አጠጣሃትም፥ ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛህ፥ የእግዚአብሔር ወንዝ ውኃን የተመላ ነው፥ ምግባቸውን አዘጋጀህ፥ እንዲሁ ታሰናዳለህና።


ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ፥ እግዚአብሔርም ባረከው።


ይስሐቅ ስለ መጪው ነገር ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው።


በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፥ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ ውቤ ሆይ፥ ነዪ።


ርብቃም ከእርሷ ዘንድ በቤት የነበረችውን የታላቁን ልጇን የዔሳውን መልካሙን ልብስ አመጣች፥ ታናሹን ልጇን ያዕቆብንም አለበሰችው፥


አባቱ ይስሐቅም፦ “ልጄ ሆይ፥ ወደ እኔ ቅረብ ሳመኝም” አለው።


የእስራኤልም ዐይኖች ከሽምግልና የተነሣ ደክመው ነበር፥ ማየትም አይችልም ነበር፥ ወደ እርሱም አቀረባቸው፥ ሳማቸውም፥ አቀፋቸውም።


ስለ ዮሴፍም እንዲህ አለ፥ “ምድሩ ከጌታ ዘንድ የተባረከ ይሁን፤ ከሰማያት በሚዘንበው የላቀ ስጦታ፥ ከታችም ከጥልቀት ከሚገኘው ውሃ፥


አባቱ ይስሐቅም መለሰ አለውም፦ “እነሆ፥ መኖሪያህ ከምድር ስብ ከላይ ከሚገኝ ከሰማይም ጠል ይሆናል፥


ያዕቆብም ዮሴፍን ባረከ እንዲህም አለ፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ እግዚአብሔር፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios