“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ዘፍጥረት 26:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊው የብኤልን ልጅ ዮዲትን፥ የኬጢያዊው የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሳው አርባ ዓመት በሆነው ጊዜ፣ የኬጢያዊውን የብኤሪን ልጅ ዮዲትን እንዲሁም የኬጢያዊውን የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትን አገባ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የሒታውያዊ የብኤሪን ልጅ ዮዲትን፥ የሒታውያዊ የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሳው አርባ ዓመት ሲሆነው የብኤሪን ልጅ ዮዲትንና የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ፤ ሁለቱም ሒታውያን ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የኬጢያዊ የብኤሪን ልጅ ዮዲትን የኬጢያዊ የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ |
“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ርብቃም ይስሐቅን አለችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”
ዔሳው ወደ ይስማኤል ሄደ፤ ቤሴሞትንም በፊት ካሉ ሚስቶቹ ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ ወሰዳት፤ እርስዋም የናኮር ወንድም የአብርሃም ልጅ የሆነው የይስማኤል ልጅና የናቡዓት እኅት ናት።
ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ የኬጤያዊውን የዔሎን ልጅ ሐዳሶን፥ የኤውያዊው የሴቤሶ ልጅ ሐና የወለዳትን ኤሌባማን፥
ሴቶች ልጆቻቸውምንም ከወንድ ልጆችህ፥ ሴቶች ልጆችህንም ከወንድ ልጆቻቸው ጋር እንዳታጋባ፥ ልጆቻቸውም አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ከአምላኮቻቸው በኋላ ሄደው አመንዝረውም ልጆችህን እንዳያስቱ ተጠንቀቅ።
ዳዊትም ኬጤያዊዉን አቤሜሌክንና የሶርህያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፥ “ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚገባ ማን ነው?” ብሎ ጠየቃቸው፤ አቢሳም፥ “እኔ ከአንተ ጋር እገባለሁ” አለ።