ዘፍጥረት 25:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ዔሳውን፥ “ዛሬ ብኵርናህን ስጠኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም፣ “በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም፥ “በመጀመሪያ ብኩርናህን ሽጥልኝ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም “መጀመሪያ ብኲርናህን ሽጥልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም፦ በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ አለው። |
ዔሳውም አለ፥ “በእውነት ስሙ ያዕቆብ ተባለ፤ ሁለት ጊዜ አሰናክሎኛልና፤ መጀመሪያ ብኵርናዬን ወሰደ፤ አሁንም እነሆ በረከቴን ወሰደ።” ዔሳውም አባቱን አለው፥ “ደግሞም አባቴ ሆይ፥ ለእኔ በረከትን አላስቀረህልኝምን?”
አለውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ታግለህ በርትተሃልና።”
የእስራኤልም በኵር የሮቤል ልጆች እነዚህ ናቸው። እርሱ የበኵር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ አባቱ ምንጣፍ ስለ ወጣ አባቱ እስራኤል በረከቱን ለልጁ ለዮሴፍ ሰጠ፤ ብኵርናም አልተቈጠረለትም።
ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤
ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኀይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው።