ዘፍጥረት 24:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አለው፥ “አንተ የእግዚአብሔር ቡሩክ፥ ግባ ስለምን አንተ በውጪ ቆመሃል? እኛም ቤትን፥ ለግመሎችህም ማደሪያን አዘጋጅተናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱንም “አንተ የእግዚአብሔር ቡሩክ ሆይ፤ ና፤ እዚህ ውጭ የቆምኸው ለምንድን ነው? እነሆ፤ ለአንተ ማረፊያ ለግመሎችህም ማደሪያ አዘጋጅቻለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም አለው፦ “አንተ የእግዚአብሔር ቡሩክ ግባ፥ ስለምን አንተ በውጪ ቆመሃል? እኔም ቤቱን ለግመሎችህም ስፍራ አዘጋጅቼአለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ላባ “አንተ እግዚአብሔር የባረከህ ሰው፥ ና ወደ ቤት እንሂድ፤ በውጪ የቆምከው ለምንድን ነው? በቤታችን ለአንተ ማረፊያ ስፍራ አለ፤ ለግመሎችህም ማደሪያ የተዘጋጀ ቦታ አለ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም አለው፦ አንተ የእግዚአብሔር ቡሩክ ግባ፤ ስለምን አንተ በውጪ ቆመሃል? እኔም ቤቱን ለግመሎችህም ስፍራ አዘጋጅቼአለሁ። |
አላቸውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪያችሁ ቤት ገብታችሁ እደሩ፤ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገም ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም” አሉት።
ጉትቻውንና አምባሮቹን በእኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእኅቱንም የርብቃን ነገር፦ ያ ሰው እንዲህ አለኝ ያለችውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደዚያ ሰው መጣ፤ እነሆም በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር።
አምላክህ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር እንደ አለ በአየን ጊዜ በአንተና በእኛ መካከል መሐላ ይሁን፤ አንተ በእኛ ላይ ክፉ እንዳታደርግ፤ እኛም በአንተ ላይ ክፉ እንዳናደርግ እንማማላለን።”
ላባም የእኅቱን የርብቃን ልጅ የያዕቆብን ስም በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ሮጠ፥ አቅፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገባው። ነገሩንም ሁሉ ለላባ ነገረው።
እናቱንም፥ “ከአንቺ ዘንድ የተሰረቀው፥ የረገምሽበትም፥ በጆሮዬም የተናገርሽበት አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር እነሆ፥ በእኔ ዘንድ አለ፤ እኔም ወስጄው ነበር” አላት። እናቱም፥ “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለችው።
ቦዔዝም አላት፦ ልጄ ሆይ፥ በእግዚአብሔር የተባረክሽ ሁኚ፣ ባለጠጋም ድሀም ብለሽ ጐበዛዝትን አልተከተልሽምና ከፊተኛው ይልቅ በመጨረሻው ጊዜ ቸርነት አድርገሻል።