አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ፤ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፤ የናኮርም ሚስት የአራን ልጅ ሚልካ ናት፤ አራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነው።
ዘፍጥረት 24:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለችውም፥ “እኔ ሚልካ ለናኮር የወለደችለት የባቱኤል ልጅ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፣ “እኔ፣ ሚልካ ለናኮር የወለደችለት፣ የባቱኤል ልጅ ነኝ” አለችው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለችውም፦ “እኔ ሚልካ ለናኮር የወለደችው የባቱኤል ልጅ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም “የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ ባቱኤልም ሚልካ ለናኮር የወለደችለት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለችውም፦ እኔ ሚልካ ለናኮር የወለደችው የባቱኤል ልጅ ነኝ |
አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ፤ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፤ የናኮርም ሚስት የአራን ልጅ ሚልካ ናት፤ አራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነው።
እንዲህም ሆነ፤ ከዚህ ነገር በኋላ ለአብርሃም እንዲህ ተብሎ ተነገረ፥ “እነሆ፥ ሚልካ ደግሞ ለወንድምህ ለናኮር ልጆችን ወለደች፤
እንደዚህ በልቡ ያሰበውን መናገሩን ሳይፈጽም እንዲህ ሆነ፦ የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት የሚልካ ልጅ የባቱኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እንስራዋንም በጫንቃዋ ተሸክማ ነበር።
እኔም “አንቺ የማን ልጅ ነሽ? ንገሪኝ” ብዬ ጠየቅኋት። እርስዋም፥ “ሚልካ የወለደችለት የናኮር ልጅ የባቱኤል ልጅ ነኝ” አለችኝ፤
እነርሱም፥ “እኛ ከካራን ነን” አሉት። “የናኮርን ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን?” አላቸው። እነርሱም፥ “እናውቀዋለን” አሉት።