La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“አይ​ደ​ለም፥ ጌታዬ፥ ቀር​በህ ስማኝ፤ እር​ሻ​ውን፥ በው​ስ​ጡም ያለ​ውን ዋሻ​ውን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በወ​ገኔ ልጆች ፊት ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ሬሳ​ህን ቅበር።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እንዲህ አይደለም ጌታዬ፤ ስማኝ፤ ዕርሻውን በውስጡ ካለው ዋሻ ጋራ ውሰደው። እነሆ፤ በወገኖቼ ኬጢያውያን ፊት ሰጥቼሃለሁ፤ ሬሳህን ቅበርበት።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“አይደለም፥ ጌታዬ፥ ስማኝ፥ እርሻውን በክልሉ ውስጥ ካለው ዋሻ ጋር ሰጥቼሃለሁ፤ ሙታንህን እንድትቀብርበት በወገኖቼ በሒታውያን ፊት ሰጥቼሃለሁ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ጌታው ስማ፤ እርሻውን በክልሉ ውስጥ ካለው ዋሻ ጋር ሰጥቼሃለሁ፤ ሙታንህን እንድትቀብርበት በወገኖቼ በሒታውያን ፊት ሰጥቼሃለሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ አይደለም ጌታዬ ስማኝ። እርሻውን ሰጥቼሃለሁ በእርሱም ዳር ያለውን ዋሻ ሰጥቼሃለሁ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼሃለሁ፤ ሬሳህን ቅበር።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 23:11
15 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም በሀ​ገሩ ሕዝብ ሁሉ ፊት ሰገደ፤


በኬጢ ልጆ​ችና በከ​ተ​ማ​ዪቱ በር በሚ​ገቡ ሁሉ ፊት ለአ​ብ​ር​ሃም ርስቱ ሆነ።


“አይ​ሆ​ንም፥ ጌታ ሆይ፥ ስማን፤ አንተ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለእኛ ንጉሥ ነህና ከመ​ቃ​ብር ስፍ​ራ​ችን በመ​ረ​ጥ​ኸው ቦታ ሬሳ​ህን ቅበር፤ ሬሳ​ህን በዚያ ትቀ​ብር ዘንድ ከእኛ መቃ​ብ​ሩን የሚ​ከ​ለ​ክ​ልህ የለም።”


ጻድ​ቃን ግን ጥበ​ብን ይመ​ክ​ራሉ፤ ምክ​ራ​ቸ​ውም ትጸ​ና​ለች።


ነፍሰ ገዳይ ሁሉ በም​ስ​ክ​ሮች ቃል ይገ​ደ​ላል፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን ማና​ቸ​ው​ንም ሰው መግ​ደል አይ​ገ​ባም።


ከዚያ የቆ​ሙ​ት​ንም፦ ይህን ምናን ከእ​ርሱ ተቀ​ብ​ላ​ችሁ ዐሥር ምናን ላለው ስጡት አላ​ቸው።


በሁ​ለት ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ሞት የሚ​ገ​ባ​ቸው ይገ​ደሉ፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን አይ​ገ​ደሉ።


“ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማ​ድ​ረ​ግም ስለ​ሚ​ሠ​ራት ኀጢ​አት ሁሉ በማ​ንም ላይ አንድ ምስ​ክር አይ​ሁን፤ በሁ​ለት ምስ​ክ​ሮች ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ቃል ነገር ሁሉ ይጸ​ናል።


ቦዓዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ፦ አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።


በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ሽማግሌዎቹም፦ እኛ ምስክሮች ነን፣ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፣ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተ ልሔም ይጠራ።


እኔም በዚህ በተቀመጡት በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት እንድትገዛው አስታውቅህ ዘንድ አሰብሁ። መቤዠት ብትወድድ ተቤዥው፣ መቤዥት ባትወድድ ግን ከአንተ በቀር ሌላ ወራሽ የለምና፥ እኔም ከእንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ አለው። እርሱም፦ እቤዥዋለሁ አለው።


ቦዔዝም ሽማግሌዎችንና ሕዝቡን ሁሉ፦ ለአቤሜሌክና ለኬሌዎን ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እንደ ገዛሁ እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ።