ዘፍጥረት 21:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕፃኑም አደገ፤ ጡትንም አስጣሉት፤ አብርሃምም ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣን አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕፃኑ አደገ፤ ጡት መጥባቱንም ተወ። አብርሃምም ይሥሐቅ ጡት በጣለባት ዕለት ታላቅ ድግስ ደገሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕፃኑም አደገ፥ ጡትንም ከመጥባት ተቋረጠ፥ አብርሃምም ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣን አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጁም አድጎ ጡት መጥባት ተወ፤ ጡት ባስጣሉበትም ቀን አብርሃም ታላቅ ግብዣ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕፃኑም አደገ ጡትንም ከመጥባት ተቋረጠ፤ አብርሃምም ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣን አደረገ። |
እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን ፈርዖን የተወለደበት ዕለት ነበር፤ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ፤ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ዐሰበ።
አበኔርም ከሃያ ሰዎች ጋር ወደ ዳዊት ወደ ኬብሮን መጣ፤ ዳዊትም ለአበኔርና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሰዎች ግብዣ አደረገላቸው።
ሰሎሞንም ነቃ፤ እነሆም፥ ሕልም ነበረ፤ ተነሥቶም ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ በጽዮንም በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አሳረገ፤ የደኅንነትንም መሥዋዕት አቀረበ፤ ለአገልጋዮቹም ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደረገ።
ሶምሶንም አላቸው፥ “እንቆቅልሽ ልስጣችሁ፤ በሰባቱም በበዓሉ ቀኖች ውስጥ ፈትታችሁ ብትነግሩኝ፥ ሠላሳ የበፍታ ቀሚስና ሠላሳ ልውጥ ልብስ እሰጣችኋለሁ፤
ሐና ግን ከእርሱ ጋር አልወጣችም። ለባልዋም፥ “ሕፃኑን ጡት እስከ አስጥለው፥ ከእኔም ጋር እስኪወጣና በእግዚአብሔር ፊት እስኪታይ ድረስ አልወጣም፤ በዚያም ለዘለዓለም ይኖራል” ብላዋለችና።
እርስዋም ከእርሱ ጋር አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ እንጀራ፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወጣች። በሴሎም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት ገባች። ልጃቸውም ከእነርሱ ጋር ነበረ።
አቤግያም ወደ ናባል መጣች፤ እነሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደርግ ነበር፤ ናባልም እጅግ ሰክሮ ነበርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለዚህም እስኪነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አልነገረችውም ነበር።