Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 14:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሶም​ሶ​ንም አላ​ቸው፥ “እን​ቆ​ቅ​ልሽ ልስ​ጣ​ችሁ፤ በሰ​ባ​ቱም በበ​ዓሉ ቀኖች ውስጥ ፈት​ታ​ችሁ ብት​ነ​ግ​ሩኝ፥ ሠላሳ የበ​ፍታ ቀሚ​ስና ሠላሳ ልውጥ ልብስ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሳምሶን እንዲህ አላቸው፤ “አንድ ዕንቈቅልሽ እነግራችኋለሁ፤ ታዲያ ፍችውን በሰርጉ በዓል ሰባት ቀኖች ውስጥ ከሰጣችሁኝ፣ ሠላሳ የቀጭን ፈትል በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ እሰጣችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሳምሶን እንዲህ አላቸው፤ “እንድ እንቈቅልሽ እነግራችኋለሁ፤ ታዲያ ፍቺውን በሰርጉ በዓል ሰባት ቀኖች ውስጥ ከሰጣችሁኝ፥ ሠላሳ የቀጭን ፈትል በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ እሰጣችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሶምሶንም እንዲህ አላቸው፤ “እስቲ ታውቁ እንደ ሆነ አንድ እንቆቅልሽ ልንገራችሁ፤ በሰባቱ የሠርጉ በዓል ቀኖች ውስጥ ይህን እንቆቅልሽ ፈትታችሁ ብትነግሩኝ፥ ሠላሳ የበፍታ ቀሚስና ሠላሳ ቅያሬ ልብስ እሰጣችኋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሶምሶንም፦ እንቆቅልሽ ልስጣችሁ፥ በሰባቱም በበዓሉ ቀኖች ውስጥ ፈትታችሁ ብትነግሩኝ፥ ሠላሳ የበፍታ ቀሚስና ሠላሳ ልውጥ ልብስ እሰጣችኋለሁ፥

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 14:12
22 Referencias Cruzadas  

ለሁ​ሉም ሁለት ሁለት መለ​ወጫ ልብስ ሰጣ​ቸው፤ ለብ​ን​ያም ግን ሦስት መቶ ብርና አም​ስት መለ​ወጫ ልብስ ሰጠው።


የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ስም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም በሰ​ማች ጊዜ ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ን​ቆ​ቅ​ልሽ ትፈ​ት​ነው ዘንድ መጣች።


እር​ሱም፥ “ሁሉ ደኅና ነው፦ አሁን ከነ​ቢ​ያት ወገን የሆኑ ሁለት ጐል​ማ​ሶች ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ወደ እኔ መጥ​ተ​ዋ​ልና፤ አንድ መክ​ሊት ብርና ሁለት መለ​ወጫ ልብስ ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ ብሎ ጌታዬ ላከኝ” አለው።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ ንዕ​ማ​ንን፥ “ሂድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ደብ​ዳቤ እል​ካ​ለሁ” አለው። እር​ሱም ሄደ፤ ዐሥ​ርም መክ​ሊት ብር፥ ስድ​ስት ሺህም ወቄት ወርቅ፥ ዐሥ​ርም መለ​ወጫ ልብስ በእጁ ወሰደ።


ሰሎ​ሞ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆኑ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያሉ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ በዚያ ጊዜ ሰባት ቀን በዓል አደ​ረጉ።


በላይ ያለ​ውን ሰማ​ይን ምድ​ር​ንም በሕ​ዝቡ ለመ​ፍ​ረድ ይጠ​ራል፥


ምሳሌንና የተሸሸገውን ነገር፥ የጠቢባንን ቃልና ዕንቈቅልሾችን ያውቃል።


“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ምሳሌ መስ​ለህ ንገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦


እኔም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህ አይ​ሁን አልሁ፤ እነ​ርሱ ግን፦ ይህ የነ​ገ​ረን ምሳሌ አይ​ደ​ለ​ምን? ይሉ​ኛል።”


ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ።


ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም “በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።


ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፤


“ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤


በምሳ ላይ ለነ​በ​ሩ​ትም ወደ ላይ​ኛው ወን​በር ሲሽ​ቀ​ዳ​ደሙ ባያ​ቸው ጊዜ ምሳሌ መስሎ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ ዛሬ ገል​ጠህ ትና​ገ​ራ​ለህ፤ ምንም በም​ሳሌ የተ​ና​ገ​ር​ኸው የለም።


አሁን ግን ታወ​ቀኝ፤ በግ​ል​ጥም ተረ​ዳኝ፤ በመ​ስ​ታ​ወ​ትም እን​ደ​ሚ​ያይ ሰው ዛሬ በድ​ን​ግ​ዝ​ግ​ዝታ እና​ያ​ለን፤ ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እና​ያ​ለን፤ አሁን በከ​ፊል፥ ኋላ ግን እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ መጠን ሁሉን አው​ቃ​ለሁ።


ሀብታችሁ ተበላሽቶአል፤ ልብሳችሁም በብል ተበልቶአል።


ከዚ​ህም በኋላ ፈር​ተው ሠላሳ ሰዎ​ችን በእ​ርሱ ላይ ሾሙ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ተቀ​መጡ።


መፍ​ታት ባት​ችሉ ግን እና​ንተ ለእኔ ሠላሳ የበ​ፍታ ቀሚ​ስና ሠላሳ ልውጥ ልብስ ትሰ​ጡ​ኛ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “ምሳ​ሌ​ህን መስ​ልና እን​ስ​ማህ” አሉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos