ዘፍጥረት 20:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ሚስቱን ሣራን “እኅቴ ናት” አላቸው፤ የከተማዪቱ ሰዎች ስለ እርስዋ እንዳይገድሉት “ሚስቴ” ናት ማለትን ፈርቶአልና፤ የጌራራ ንጉሥ አቤሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም አብርሃም ሚስቱን ሣራን፣ “እኅቴ ናት” ይል ነበር። ስለዚህ የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ መልእክተኛ ልኮ ሣራን ወሰዳት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃም ሚስቱን ሣራን፦ “እኅቴ ናት” አለ፥ የገራርም ንጉሥ አቢሜሌክ በመልክተኛ ሣራን ወሰዳት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃም ሚስቱን ሣራን እኅቴ ናት አለ፤ ስለዚህ የገራራ ንጉሥ አቤሜሌክ ሰዎች ልኮ ሣራን እንዲያመጡለት አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ሚስቱን ሣራም፤ እኅቴ ናት አለ የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት። |
በዚያ ዘመን አቤሜሌክ፥ ሚዜው አኮዘትና የሠራዊቱ አለቃ ፋኮል ወደ አብርሃም ሄደው አሉት፥ “በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤
በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ሌላ ራብ ሆነ፤ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወደ አቤሜሌክ ወደ ጌራራ ሄደ።
ነቢዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን፥ “ኀጢአተኛውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔር የሚጠላውን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ መጥቶብሃል።
የማርሶስ ሰው የኢያድያ ልጅ አልዓዛር፥ “ከአካዝያስ ጋር ተባብረሃልና እግዚአብሔር ሥራህን አፍርሶታል” ብሎ በኢዮሣፍጥ ላይ ትንቢት ተናገረ። መርከቦቹም ተሰበሩ፤ ወደ ተርሴስም ይሄዱ ዘንድ አልቻሉም።
ነገር ግን የባቢሎን መሳፍንት መልእክተኞች በሀገሩ ላይ ስለ ተደረገው ተአምራት ይጠይቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተላኩ ጊዜ እግዚአብሔር ይፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።