እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ከሀገርህ፥ ከዘመዶችህም፥ ከአባትህም ቤት ተለይተህ ውጣ፤ እኔ ወደማሳይህም ምድር ሂድ።
ዘፍጥረት 20:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኋት፥ ‘ይህን ጽድቅ አድርጊልኝ፤ በገባንበት ሀገር ሁሉ ወንድሜ ነው በዪ።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አዝዞኝ ከአባቴ ቤት ወጥቼ በየአገሩ ስዞር፣ ‘ለእኔ ያለሽን ፍቅር በዚህ ግለጭልኝ፤ በየደረስንበት ስፍራ ሁሉ “እርሱ ወንድሜ ነው” በዪ’ ብያት ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኋት፦ ‘በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፦ ወንድሜ ነው ብለሽ ስለ እኔ ተናገሪ።’” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤት ወጥቼ ወደ ባዕድ አገር እንድሄድ ባዘዘኝ ጊዜ ‘በምንሄድበት ቦታ ሁሉ እኅቱ ነኝ ብትዪ ለእኔ ታላቅ ውለታ እንዳደረግሽልኝ እቈጥረዋለሁ’ ብዬአት ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኍት በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፤ ወንድሜ ነው ብለሽ ስለእኔ ተናገሪ። |
እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ከሀገርህ፥ ከዘመዶችህም፥ ከአባትህም ቤት ተለይተህ ውጣ፤ እኔ ወደማሳይህም ምድር ሂድ።
እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይደለምን? እርስዋ ደግሞ ራስዋ ወንድሜ ነው አለች፤ በልቤ ቅንነትና በእጄ ንጹሕነት ይህን አደረግሁት።”
ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ ስማን።
ጴጥሮስም፥ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን መንፈስ ትፈታተኑት ዘንድ እንዴት ተባበራችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግሮች በበር ናቸው፤ አንቺንም ይወስዱሻል” አላት።
አብርሃም በተጠራ ጊዜ ርስት አድርጎ ይወርሰው ዘንድ ወዳለው ሀገር ለመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚደርስም ሳያውቅ ሄደ።