ዘፍጥረት 18:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኃ እናምጣላችሁ፤ እግራችሁንም እንጠባችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥቂት ውሃ ይምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ እዚህም ከዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ፥ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግራችሁን የምትታጠቡበት ውሃ እስካመጣላችሁ ድረስ በዚህ ዛፍ ጥላ ሥር ዐረፍ በሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፤ |
አላቸውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪያችሁ ቤት ገብታችሁ እደሩ፤ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገም ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም” አሉት።
ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፤ ግመሎቹንም አራገፈ፤ ለግመሎቹም ሣርና ገለባ አቀረቡላቸው፤ እግሩን ይታጠብ ዘንድ ውኃ አመጡለት፤ ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎችም አመጡላቸው።
ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፥ “ይህቺን ሴት ታያታለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእግሮች ውኃ ስንኳ አልሰጠኸኝም፤ እርስዋ ግን አልቅሳ በእንባዋ እግሬን አራሰች፤ በጠጕርዋም አበሰች።
ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።
ተነሥታም በግንባርዋ በምድር ወድቃ ሰገደችና፥ “እነሆ፥ እኔ ገረድህ የጌታዬን ሎሌዎች እግር አጥብ ዘንድ አገልጋይ ነኝ” አለች።