እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸቷ ይፈጽሙአት እንደ ሆነ አይ ዘንድ እወርዳለሁ፤ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ።”
ዘፍጥረት 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የሰዎች ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን ሰዎቹ ይሠሩ የነበሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሰዎቹ ይሠሩአቸው የነበሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። |
እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸቷ ይፈጽሙአት እንደ ሆነ አይ ዘንድ እወርዳለሁ፤ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ።”
በሦስተኛውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና ለሦስተኛው ቀን ተዘጋጅተው ይጠብቁ።
እግዚአብሔርም በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጽመው ደነገጡ።
ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም ሀገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊዪቱና ወደ መልካሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
እኛን በሚቈጣጠር በእርሱ በዐይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው እንጂ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።