ዘፍጥረት 10:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምስራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካም ልጆች፦ ኵሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካም ልጆች፦ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ እና ከነዓን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የካም ልጆች፦ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥና ከነዓን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፋጥ፥ ከነዓን ናቸው። |
በዚያም የሚያበራ ዕንቍና የሚያብረቀርቅ ዕንቍ አለ። የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል፤
ብዙና እጅግ ያማረ መሰማርያም አገኙ፤ ምድሪቱም በፊታቸው ሰፊና ጸጥተኛ ሰላም ያላትም ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ።
እንዳያጠፋቸው የቍጣውን መቅሠፍት ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ባጠፋቸው ነበር አለ።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከባቢሎንና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላሜጤን፥ ከምሥራቅና ከምዕራብ ለቀሩት ለሕዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
በፈረሶች ተቀመጡ፤ ሰረገሎችንም አዘጋጁና ውጡ፤ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የሊብያ ኀያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኀያላን ይውጡ።
ፋርስና ሉድ፥ ሊብያም በሠራዊትሽ ውስጥ ሰልፈኞችሽ ነበሩ፤ ጋሻና ራስ ቍርም በአንቺ ውስጥ ያንጠለጥሉ ነበር፤ እነርሱም ክብርሽን ሰጡ።