Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 5:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ለኖ​ኅም አም​ስት መቶ ዓመት ሆነው፤ ኖህም ሦስት ልጆ​ችን ወለደ፤ እነ​ር​ሱም ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ኖኅ ዕድሜው 500 ዓመት ሲሆን ሴምን፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ኖኅም ሴምን፥ ካምን እና ያፌትን ወለደ፤ ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ኖኅ 500 ዓመት ከሆነው በኋላ ሦስት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ እነርሱም ሴም፥ ካምና ያፌት ይባሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ፤ ኖኅም ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 5:32
13 Referencias Cruzadas  

ለሴ​ምም ደግሞ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እር​ሱም የያ​ፌት ታላቅ ወን​ድ​ምና የዔ​ቦር ልጆች ሁሉ አባት የሆ​ነው ነው።


ኖኅም ሦስት ልጆ​ችን ሴምን፥ ካምን ያፌ​ት​ንም ወለደ።


የቃ​ይ​ናን ልጅ፥ የአ​ር​ፋ​ክ​ስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላ​ሜሕ ልጅ፥


የኖኅ የል​ጆቹ ነገ​ዶች እንደ ትው​ል​ዳ​ቸው በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ዚ​ህም ከጥ​ፋት ውኃ በኋላ ሕዝ​ቦች በም​ድር ላይ ተዘሩ።


የኖኅ ልጆች የሴም፥ የካ​ምና፥ የያ​ፌት ትው​ልድ ይህ ነው፤ ከጥ​ፋት ውኃም በኋላ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ላ​ቸው።


በዚ​ያ​ውም ቀን ኖኅ ወደ መር​ከብ ገባ፤ የኖኅ ልጆ​ችም ሴም፥ ካም፥ ያፌ​ትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስ​ቱም የል​ጆቹ ሚስ​ቶች ከእ​ርሱ ጋር ገቡ።


ላሜ​ሕም የኖ​ረ​በት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሰዎች በም​ድር ላይ መብ​ዛት በጀ​መሩ ጊዜ መልከ መል​ካ​ሞች ሴቶች ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ላ​ቸው፤


ኖኅም የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ በሆነ ጊዜ የስ​ድ​ስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ።


የካ​ምም ልጆች ኩሽ፥ ምስ​ራ​ይም፥ ፉጥ፥ ከነ​ዓን ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios