ፈሪሳዊውም ቆመና እንዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማኞችና እንደ ዐመፀኞች፥ እንደ አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ያላደረግኸኝ አመሰግንሃለሁ።
ገላትያ 6:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዱም ምንም ሳይሆን ምንም የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው ምንም ሳይሆን ትልቅ የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰው ምንም ሳይሆን አንድ ነገር የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው ከሌሎች የሚሻልበት ነገር ሳይኖረው “እኔ ከሌሎች እበልጣለሁ” ብሎ ቢያስብ ራሱን ያታልላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱ ምንም ሳይሆን ምንም የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና። |
ፈሪሳዊውም ቆመና እንዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማኞችና እንደ ዐመፀኞች፥ እንደ አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ያላደረግኸኝ አመሰግንሃለሁ።
ቀድሞም ከዚህ ዘመን በፊት ቴዎዳስ ተነሥቶ ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፤ አራት መቶ ሰዎችም ተከተሉት፤ ነገር ግን እርሱም ጠፋ፤ የተከተሉትም ሁሉ ተበታተኑ፤ እንደ ኢምንትም ሆኑ።
እርስ በርሳችሁም በአንድ ዐሳብ ተስማሙ፤ ትዕቢትን ግን አታስቡ፤ ራሱን የሚያዋርደውንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋቆች ነን አትበሉ።
በተሰጠኝ በእግዚአብሔር ጸጋ ሁላችሁም እንዳትታበዩ እነግራችኋለሁ፤ ራሳችሁን ከዝሙት የምታነጹበትን ዐስቡ እንጂ ትዕቢትን አታስቡ፤ ሁሉም እንደ እምነቱ መጠን እግዚአብሔር እንደ አደለው ይኑር።
ትንቢት ብናገር፥ የተሰውረውን ሁሉ፥ ጥበብንም ሁሉ ባውቅ፥ ተራራ እስከ ማፍለስ የሚያደርስ ፍጹም እምነትም ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
ራሳችሁን አታስቱ፤ ከመካከላችሁ በዚህ ዓለም ጥበበኛ እንደ ሆነ የሚያስብ ሰው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላዋቂ ያድርግ።
እነሆ እናንተ ስላገበራችሁኝ በመመካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእኔማ በእናንተ ዘንድ ልከብርና እናንተም ምስክሮች ልትሆኑኝ ይገባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢምንት ብሆንም ዋናዎቹ ሐዋርያት ሁሉ ከሠሩት ሥራ ያጐደልሁባችሁ የለምና።
አለቆች የመሰሉት ግን ቀድሞ እነርሱ እንዴት እንደ ነበሩ ልናገር አያገደኝም፤ እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና፤ አለቆች የመሰሉትም ከራሳቸው ምንም ነገር የጨመሩልኝ የለምና።
የሰጠኝንም ጸጋ ዐውቀው አዕማድ የሚሏቸው ያዕቆብና ኬፋ፥ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ፥ እነርሱም ወደ አይሁድ እንድንሄድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን።