Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 5:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ቀድ​ሞም ከዚህ ዘመን በፊት ቴዎ​ዳስ ተነ​ሥቶ ራሱን ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ አራት መቶ ሰዎ​ችም ተከ​ተ​ሉት፤ ነገር ግን እር​ሱም ጠፋ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​ትም ሁሉ ተበ​ታ​ተኑ፤ እንደ ኢም​ን​ትም ሆኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ከዚህ ቀደም፣ ቴዎዳስ ራሱን ትልቅ አድርጎ በመቍጠር ተነሥቶ፣ አራት መቶ ያህል ሰዎች ተባበሩት፤ ነገር ግን እርሱም ተገደለ፤ ተከታዮቹም ሁሉ ተበታተኑ፤ ነገሩም እንዳልነበር ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ ‘እኔ ታላቅ ነኝ፤’ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፤ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ፤ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ፤ እንደ ምናምንም ሆኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ከዚህ በፊት ቴዎዳስ የሚባል ሰው ‘እኔ ትልቅ ሰው ነኝ’ ብሎ ተነሥቶ ነበር፤ አራት መቶ የሚያኽሉም ሰዎች ከእርሱ ጋር ተባብረው ነበር። ነገር ግን እርሱ ተገደለ፤ ተከታዮቹ ተበታተኑ፤ ዓላማውም እንዳልነበረ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ፦ “እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፥ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፥ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 5:36
14 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያ​ችም ከተማ ሲሞን የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ የሰ​ማ​ርያ ሰዎ​ች​ንም ያስት ነበር፤ ሰው​የዉ ሥራ​የኛ ነበር፤ ራሱ​ንም ታላቅ ያደ​ርግ ነበር።


ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል፤ በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል።


በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም “ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት” ተብሎ ተጻፈ።


እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።


አን​ዱም ምንም ሳይ​ሆን ምንም የሆነ ቢመ​ስ​ለው ራሱን ያታ​ል​ላ​ልና።


አለ​ቆች የመ​ሰ​ሉት ግን ቀድሞ እነ​ርሱ እን​ዴት እንደ ነበሩ ልና​ገር አያ​ገ​ደ​ኝም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ፊት አያ​ዳ​ላ​ምና፤ አለ​ቆች የመ​ሰ​ሉ​ትም ከራ​ሳ​ቸው ምንም ነገር የጨ​መ​ሩ​ልኝ የለ​ምና።


“ምና​ል​ባት ከዚህ በፊት ወን​ጀል የሠ​ራ​ህና ከነ​ፍሰ ገዳ​ዮች አራት ሺህ ሰዎ​ችን ይዘህ ወደ ምድረ በዳ የወ​ጣህ ያ ግብ​ፃዊ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?” አለው።


ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።


በመንፈስም ወደ በረሓ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።


ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፤ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ።


እንግዲህ ‘እነሆ፥ በበረሀ ነው፤’ ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ ‘እነሆ፥ በእልፍኝ ነው፤’ ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤


ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ፤’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ በእ​ነ​ዚህ ሰዎች በም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios