ገላትያ 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ በትውልዳችን አይሁድ ነን፤ ኀጢአተኞች የሆኑ አሕዛብም አይደለንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኛ በትውልዳችን አይሁድ እንጂ፣ ‘ኀጢአተኞች አሕዛብ’ ያልሆንን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ በፍጥረት አይሁድ ነን፤ ከኃጢአተኞች አሕዛብ አይደለንም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርግጥ እኛ በትውልዳችን አይሁድ ነን፤ እንደ ኃጢአተኞች አሕዛብም አይደለንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ በፍጥረት አይሁድ ነን ኃጢአተኞችም የሆኑ አሕዛብ አይደለንም፤ |
የሰው ልጅ በኀጢኣተኞች ሰዎች እጅ ተላልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው፤ ይሰቅሉታል፤ ይገድሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።” 10፥33-34፤ ሉቃ. 9፥22፤ 18፥31-33።
እንግዲህ ምን እንላለን? ከእነርሱ እንበልጣለን? አይደለም፤ አይሁዳዊንም፥ አረማዊንም እነሆ፥ አስቀድመን ነቅፈናቸዋል፤ ሁሉም ስተዋልና።
ስለዚህም እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ የሰጠው ተስፋ የታመነ ይሆን ዘንድ፥ የሚጸድቁ በእምነት እንጂ የኦሪትን ሥራ በመፈጸም ብቻ እንዳይደለ ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ጽድቅን በእምነት አደረገ።
በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንሻ እኛ እንደ ኀጢአተኞች ከሆን እንግዲህ ክርስቶስ የኀጢአት አገልጋይ መሆኑ ነውን? አይደለም።
እኛ ሁላችን ቀድሞ እንደ ሥጋችን ምኞት ኖርን፤ የሥጋችንንም ፈቃድና ያሰብነውን አደረግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥአንም ሁሉ የጥፋት ልጆች ሆንን።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
እግዚአብሔርም፦ ሄደህ ኀጢኣተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፤ እስኪጠፉም ድረስ ውጋቸው ብሎ በመንገድ ላከህ።