Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ገላትያ 2:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በክ​ር​ስ​ቶስ ልን​ጸ​ድቅ የም​ንሻ እኛ እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ከሆን እን​ግ​ዲህ ክር​ስ​ቶስ የኀ​ጢ​አት አገ​ል​ጋይ መሆኑ ነውን? አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “በክርስቶስ ለመጽደቅ ስንፈልግ፣ እኛ ራሳችን ኀጢአተኞች መሆናችን ግልጽ ነው፤ ታዲያ ክርስቶስ ኀጢአት እንዲስፋፋ ያደርጋልን? ከቶ አይሆንም!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ነገር ግን በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ፥ እኛ ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ብንገኝ፥ ታዲያ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነውን? በጭራሽ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በክርስቶስ በማመን ለመጽደቅ ስንፈልግ እኛ ራሳችን ኃጢአተኞች ሆነን ብንገኝ ታዲያ፥ ኃጢአት እንድንሠራ የሚያደርገን ክርስቶስ ነው ማለት ነውን? ከቶ አይደለም!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ነገር ግን በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ ስንሆን ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ከተገኘን፥ እንግዲያስ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነዋ? አይደለም።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 2:17
17 Referencias Cruzadas  

ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”


የወ​ይኑ ባለ​ቤት በመጣ ጊዜ እን​ግ​ዲህ ምን ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል? ይመ​ጣል፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ገባ​ሮች ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ወይ​ኑ​ንም ለሌ​ሎች ገባ​ሮች ይሰ​ጣል፤” ቃሉ​ንም ሰም​ተው፥ “አይ​ሆ​ንም፤ እን​ዲህ አይ​ደ​ረ​ግም” አሉ።


እን​ግ​ዲህ ምን​ድን ነው? እስ​ራ​ኤል የፈ​ለ​ገ​ውን አላ​ገ​ኘም። የተ​መ​ረ​ጠው ግን አግ​ኝ​ቶ​አል፤ የቀ​ሩ​ትም ታወሩ።


እን​ግ​ዲህ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እው​ነት ለማ​ድ​ረግ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም ተስፋ ያጸና ዘንድ ለግ​ዝ​ረት መል​እ​ክ​ተና ሆነ እላ​ለሁ።


መጽ​ሐፍ፥ “በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ፥ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተና​ገረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰ​ተና ነውና።


እን​ዲ​ህማ ከሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ለም እን​ደ​ምን ይፈ​ር​ዳል?


ነገር ግን ኬፋ ወደ አን​ጾ​ኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃ​ወ​ም​ሁት፤ ነቅ​ፈ​ውት ነበ​ርና።


እኛ በት​ው​ል​ዳ​ችን አይ​ሁድ ነን፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞች የሆኑ አሕ​ዛ​ብም አይ​ደ​ለ​ንም።


እን​ግ​ዲህ ኦሪት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ውን ተስፋ ልት​ከ​ለ​ክል መጣ​ችን? አይ​ደ​ለም፤ ማዳን የሚ​ቻ​ለው ሕግ ተሠ​ርቶ ቢሆ​ንማ፥ በእ​ው​ነት በዚያ ሕግ ጽድቅ በተ​ገኘ ነበር።


እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መስ​ቀል እንጂ በሌላ አል​መ​ካም፤ በእኔ ዘንድ ዓለሙ የሞተ ነው፥ እኔም በዓ​ለሙ ዘንድ የሞ​ትሁ ነኝ።


እር​ሱም የመ​ቅ​ደ​ስና የእ​ው​ነ​ተ​ኛ​ይቱ ድን​ኳን አገ​ል​ጋይ ነው፤ እር​ስ​ዋም በሰው ሳይ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ተ​ከ​ለች ናት።


እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos