በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአባቶች ቤቶች አለቆች አያሌዎች ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው ይሠሩት ዘንድ በፈቃዳቸው ሰጡ።
ዕዝራ 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሪያዎቹ ነንና፥ አምላካችን ግን በባርነታችን አልተወንም፤ ቀለባችንን ይሰጡን ዘንድ፥ የአምላካችንንም ቤት ከፍ ከፍ ያደርጉ ዘንድ፥ የተፈታውንም ይጠግኑ ዘንድ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም ቅጥር ያደርጉልን ዘንድ በፋርስ ነገሥታት ፊት ሞገስን ሰጠን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሮች ብንሆንም፣ አምላካችን ግን ባሮች ሆነን እንድንቀር አልተወንም፤ ነገር ግን በፋርስ ነገሥታት ፊት ቸርነቱን አሳየን፤ የአምላካችንን ቤት እንደ ገና እንድንሠራና ፍርስራሾቿን እንድንጠግን አዲስ ሕይወት ሰጠን፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም የመከላከያ ቅጥር ሰጠን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያዎች ነን፥ አምላካችን ግን በባርነታችን አልተወንም፥ የአምላካችንን ቤት እንድንሠራና ፍርስራሾቹን እንድንጠግን መታደስን ሊሰጠን፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም ግንብ ሊሰጠን በፋርስ ነገሥታት ፊት ፅኑ ፍቅሩን በእኛ ላይ ዘረጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ ባርያዎች ነበርን፤ አንተ ግን ባርያዎች ሆነን እንድንቀር አልተውከንም፤ አንተ የፋርስ ነገሥታት እንዲራሩልንና በሕይወት ነጻ ወጥተን ቀደም ሲል ፈርሶ የነበረውን ቤተ መቅደስህን እንደገና መልሰን እንድንሠራ፥ እዚህም በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሰላም እንድንኖር ፈቀድክልን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎች ነንና፥ አምላካችን ግን በባርነታችን አልተወንም፤ የሕይወት መታደስን ይሰጠን ዘንድ፥ የአምላካችንንም ቤት እንሠራ ዘንድ፥ የተፈታውንም እንጠግን ዘንድ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም ቅጥር ይደረግልን ዘንድ በፋርስ ነገሥታት ፊት ምሕረቱን ሰጠን። |
በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአባቶች ቤቶች አለቆች አያሌዎች ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው ይሠሩት ዘንድ በፈቃዳቸው ሰጡ።
ይህም ዕዝራ ከባቢሎን ወጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአምላኩም የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ ያሻውን ሁሉ ሰጠው።
እኔም፥ “እኛ ያለንበትን ጕስቍልና፥ ኢየሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ። አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ” አልኋቸው።
ለመስማትም እንቢ አሉ፤ ያደረግህላቸውንም ተአምራት አላሰቡም፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፤ ለባርነታቸውም ወደ ግብፅ ይመለሱ ዘንድ አለቃን ሾሙ፤ አንተ ግን መሓሪና ይቅር ባይ አምላክ፥ ለቍጣም የምትዘገይ፥ ምሕረትንም የምታበዛ ነህ፤ አልተውሃቸውም።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከኀዘንህና ከመከራህ፥ ከተገዛህለትም ከጽኑ ባርነት ያሳርፍሃል።
አጥር አጠርሁ፤ በዙሪያውም ቈፈርሁ፤ ድንጋዮችንም ለቅሜ አወጣሁ፤ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከልሁ፤ በመካከሉም ግንብ ሠራሁ፤ ደግሞም የመጥመቂያ ጕድጓድ ማስሁለት፤ ወይንንም ያፈራ ዘንድ ጠበቅሁት፤ ዳሩ ግን እሾህን አፈራ።
አሁንም በወይኔ ላይ የማደርገውን እነግራችኋለሁ፤ አጥሩን እነቅላለሁ፤ ለብዝበዛም ይሆናል፤ ቅጥሩንም አፈርሳለሁ፤ ለመራገጫም ይሆናል።
ከጥንት ጀምሮ የፈረሱትን ይሠራሉ፤ ከቀድሞ ጀምሮ የፈረሱትንም ያቆማሉ፤ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደ ገና ያድሳሉ።
ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ወደ አሕዛብ አርቄአቸዋለሁ፤ ወደ ሀገሮችም እበትናቸዋለሁ፤ ይሁን እንጂ በመጡባቸው ሀገሮች በእነዚያ ትንሽ መቅደስ እሆናቸዋለሁ በል።
እናንተ ብዙ ነገርን ተስፋ አደረጋችሁ፥ እነሆም፥ ጥቂት ሆነ፣ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት። ይህ ስለ ምንድር ነው? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ሁሉ ወደ እየቤታችሁ እየሮጣችሁ የእኔ ቤት ፈርሶ ስለ ተቀመጠ ነው።