እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላላቆች እንደ ታናናሽ ወንድሞቻቸው፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
ዕዝራ 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በንጉሡ በአርተሰስታ መንግሥት ከእኔ ጋር ከባቢሎን የወጡ የአባቶች ቤቶች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ትውልዳቸውም ይህ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ከባቢሎን ዐብረውኝ የወጡት የየቤተ ሰቡ አለቆችና ዐብረዋቸው የተመዘገቡት እነዚህ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በንጉሡ በአርጤክስስ መንግሥት ከእኔ ጋር ከባቢሎን የወጡ የአባቶች አለቆች እነዚህ ናቸው ትውልዳቸውም ይህ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ከእኔ ጋር ከባቢሎን የተመለሱት የቤተሰብ አለቆች በየትውልዳቸው እንደሚከተለው ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በንጉሡ በአርጤክስስ መንግሥት ከእኔ ጋር ከባቢሎን የወጡ የአባቶች ቤቶች አለቆች እነዚህ ናቸው። ትውልዳቸውም ይህ ነው፤ |
እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላላቆች እንደ ታናናሽ ወንድሞቻቸው፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ቃል ሁሉና በንጉሡ ትእዛዝ ሁሉ በሮቤላውያንና በጋዳውያን፥ በምናሴም ነገድ እኩሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው።
እስራኤልም ሁሉ ስለ ኀጢአታቸው ወደ ባቢሎን ከተማረኩ በኋላ፥ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
እነዚህ ከሌዋውያን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች በየትውልዳቸው አለቆች ነበሩ። እነዚህም በኢየሩሳሌም ይቀመጡ ነበር።
የይሁዳና የብንያም የአባቶች ቤቶች አለቆችም፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት ይወጡ ዘንድ እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው ሁሉ ተነሡ።
ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከሮሃልያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጎዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤
በመንግሥቴም ውስጥ ካሉ ከእስራኤል ሕዝብ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ የሚወድድ ሁሉ ከአንተ ጋር እንዲሄድ አዝዣለሁ።
በንጉሡ ፊት በሚመክሩትም፥ በኀያላኑም፥ በንጉሡ አለቆች ሁሉ ፊት በእኔ ላይ ምሕረቱን ላከ። እኔም በእኔ ላይ ባለችው በአምላኬ በእግዚአብሔር እጅ በረታሁ፤ ከእኔም ጋራ ይወጡ ዘንድ ከእስራኤል አለቆቹን ሰበሰብሁ።
ይህም ዕዝራ ከባቢሎን ወጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአምላኩም የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ ያሻውን ሁሉ ሰጠው።
ከእስራኤልም ልጆች ከካህናቱም፥ ከሌዋውያኑም፥ ከመዘምራኑም፥ ከበረኞቹም፥ ከናታኒምም በንጉሡ በአርተሰስታ በሰባተኛው ዓመት ዐያሌዎች ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።