በመንግሥቴም ውስጥ ካሉ ከእስራኤል ሕዝብ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ የሚወድድ ሁሉ ከአንተ ጋር እንዲሄድ አዝዣለሁ።
ዕዝራ 7:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በንጉሡ መንግሥትና በልጆቹ ላይ ቍጣ እንዳይሆን፥ የሰማይ አምላክ ያዘዘው ሁሉ ይደረግ፤ ለሰማይ አምላክ ቤት የታዘዘውንም እንዳታቋርጡ ተጠንቀቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰማይ አምላክ የሚያዘው ሁሉ፣ ለሰማይ አምላክ ቤተ መቅደስ በፍጹም ትጋት ይደረግ፤ በንጉሡና በልጆቹ መንግሥት ላይ ለምን ቍጣ ይውረድ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በንጉሡና በልጆቹ መንግሥት ላይ ቁጣ እንዳይሆን፥ የሰማያት አምላክ የሚያዘው ሁሉ ልክ እንዳዘዘው ለሰማያት አምላክ ቤት ይደረግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንጉሡና በልጆቹ ላይ ቊጣ እንዳይመጣ የሰማይ አምላክ ለቤተ መቅደሱ የሚያዘው ሁሉ በጥንቃቄ መፈጸም አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በንጉሡና በልጆቹ መንግሥት ላይ ቍጣ እንዳይሆን፥ የሰማይ አምላክ ያዘዘው ሁሉ ለሰማይ አምላክ ቤት በሙሉ ይደረግ። |
በመንግሥቴም ውስጥ ካሉ ከእስራኤል ሕዝብ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ የሚወድድ ሁሉ ከአንተ ጋር እንዲሄድ አዝዣለሁ።
እስከ መቶ መክሊት ብርም ቢሆን፥ እስከ መቶም የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ ዘይት ቢሆን፥ ጨውም ያለ ልክ ቢሆን፤
እነርሱም፥ “ቸነፈር ወይም ሰይፍ እንዳይጥልብን የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንድንሄድ፥ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ የዕብራውያን አምላክ ጠራን” አሉት።
በእርስዋ ሰላም፥ ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማረክኋችሁ ሀገር ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።”
በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፣ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፣ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ።