ዕዝራ 4:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህችም ከተማ የተሠራች እንደ ሆነ፥ ቅጥርዋም የታደሰ እንደ ሆነ፥ ሰላም እንደማይኖርህ ለንጉሡ እናስታውቃለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህች ከተማ ተመልሳ የምትሠራና ቅጥሮቿም እንደ ገና የሚገነቡ ከሆነ፣ ከኤፍራጥስ ማዶ ምንም ነገር እንደማይኖርህ፣ ንጉሥ ታውቅ ዘንድ እንወድዳለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህችም ከተማ ከተገነባች፥ የቅጥሮቿም ሥራ ከተጠናቀቀ፥ በወንዝ ማዶ ባለ አገር ክፍል እንደሌለህ ለንጉሡ እናስታውቃለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ፥ ይህች ከተማ እንደገና ከተሠራችና የቅጽሮችዋም ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ ግርማዊነትዎ ከኤፍራጥስ ማዶ በሚገኙት ክፍላተ ሀገሮች ላይ ምንም ይዞታ እንደማይኖርዎ እንገልጻለን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህችም ከተማ የተሠራች እንደ ሆነ፥ ቅጥርዋም የታደሰ እንደ ሆነ፥ በወንዝ ማዶ ክፍል እንደሌለህ ለንጉሡ እናስታውቃለን።” |
ከወንዙ ወዲህ ባሉት ነገሥታት ሁሉ፥ ከወንዙም ወዲህ ባለው ሀገር ሁሉ ላይ ከቲላሳ ጀምሮ እስከ ጋዛ ድረስ ነግሦ ነበር፤ በዙሪያውም ባለው በሁሉ ወገን ሰላም ሆኖለት ነበር።
በአባቶችህ ታሪክ መጽሐፍ ምርመራ ይደረግ፤ በዚያም በታሪክ መጽሐፍ ይህች ከተማ ዐመፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገሥታትንና አውራጃዎችንም እንደ ጎዳች፥ ከጥንቱም የገባሮች ሽፍትነት በእርስዋ እንደ ተጀመረ ታገኛለህ፤ ታውቃለህም፤ ስለዚህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።
ንጉሡም ለአዛዡ ለሬሁም፥ ለጸሓፊውም ለሲምሳይ፥ በሰማርያና በወንዝ ማዶም ለተቀመጡትና ለቀሩት ተባባሪዎቻቸው እንዲህ የሚለውን መልስ ላከ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን።
በኢየሩሳሌምም እጅግ ኀያላን ነገሥታት ነበሩ፤ በወንዝም ማዶ ያለውን ሀገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብርንና እጅ መንሻንም ይቀበሉ ነበር።