Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 4:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ይህች ከተማ ተመልሳ የምትሠራና ቅጥሮቿም እንደ ገና የሚገነቡ ከሆነ፣ ከኤፍራጥስ ማዶ ምንም ነገር እንደማይኖርህ፣ ንጉሥ ታውቅ ዘንድ እንወድዳለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ይህችም ከተማ ከተገነባች፥ የቅጥሮቿም ሥራ ከተጠናቀቀ፥ በወንዝ ማዶ ባለ አገር ክፍል እንደሌለህ ለንጉሡ እናስታውቃለን።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህም የተነሣ፥ ይህች ከተማ እንደገና ከተሠራችና የቅጽሮችዋም ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ ግርማዊነትዎ ከኤፍራጥስ ማዶ በሚገኙት ክፍላተ ሀገሮች ላይ ምንም ይዞታ እንደማይኖርዎ እንገልጻለን።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ይህ​ችም ከተማ የተ​ሠ​ራች እንደ ሆነ፥ ቅጥ​ር​ዋም የታ​ደሰ እንደ ሆነ፥ ሰላም እን​ደ​ማ​ይ​ኖ​ርህ ለን​ጉሡ እና​ስ​ታ​ው​ቃ​ለን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ይህችም ከተማ የተሠራች እንደ ሆነ፥ ቅጥርዋም የታደሰ እንደ ሆነ፥ በወንዝ ማዶ ክፍል እንደሌለህ ለንጉሡ እናስታውቃለን።”

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 4:16
5 Referencias Cruzadas  

ከዚህም በቀር ዳዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት መልሶ ለመያዝ በሄደ ጊዜ፣ የሱባን ንጉሥ የረአብን ልጅ አድርአዛርን ወጋው።


ከወንዙ በስተ ምዕራብ፣ ከቲፍሳ እስከ ጋዛ ያሉትን መንግሥታት ስለ ገዛ፣ በሁሉም አቅጣጫ ሰላም ሆኖለት ነበር።


ስለዚህ በአባቶችህ ቤተ መዛግብት ምርመራ ይደረግ፤ በእነዚህ መዛግብት ውስጥ ይህች ከተማ ዐመፀኛ ከተማ እንደ ሆነች፣ ነገሥታትንና አውራጃዎችን የጐዳችና ከጥንት ጀምሮ የዐመፅ ጐሬ ስለ መሆኗ ማስረጃ ታገኛለህ፤ እንግዲህ ከተማዪቱ የተደመሰሰችው በዚህ ምክንያት ነው።


ንጉሡም ይህን መልስ ላከ፤ ለአገረ ገዥው ሬሁም፣ ለጸሓፊው ሲምሳይ፣ በሰማርያና በኤፍራጥስ ማዶ ለሚኖሩ ተባባሪዎቻቸው፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን፤


ኢየሩሳሌም ከኤፍራጥስ ማዶ ያለውን አገር ሁሉ የገዙ፣ ቀረጥ፣ ግብርና እጅ መንሻም ይቀበሉ የነበሩ ኀያላን ነገሥታት ነበሯት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos