ነገር ግን አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዳላመኑ ከአባቶቻቸው አንገት ይልቅ አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙም።
ሕዝቅኤል 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እኔን ወደ አስመረሩኝ ወደ እስራኤል ቤት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፁብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በእኔ ላይ ወደ ዐመፀው፣ ወደ ዐመፀኞቹ የእስራኤል ልጆች እልክሃለሁ፤ እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐምፀውብኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ወደ እስራኤል ልጆች፥ ወደ ዓመፀኞች አገር፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በእኔ ላይ ዐመፁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት ወደ እስራኤል ሕዝብ እልክሃለሁ፤ እነርሱና የቀድሞ አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ ላይ እንዳመፁ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁ ወደ ዓመፀኞች ሰዎች ወደ እስራኤል ልጆች እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፁብኝ። |
ነገር ግን አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዳላመኑ ከአባቶቻቸው አንገት ይልቅ አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙም።
የገባላቸውንም ቃል ኪዳን ሁሉ አልጠበቁም። ከንቱ ነገርንም ተከተሉ፤ ከንቱም ሆኑ፤ እንደ እነርሱም እንዳይሠሩ ያዘዛቸውን በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብ ተከተሉ።
ከአባቶቻችን ዘመን ጀምረን እስከ ዛሬ ድረስ እጅግ በድለናል፤ ስለ ኀጢአታችን እኛና ልጆቻችን ንጉሦቻችን፥ ካህናቶቻችንም ለሰይፍና ለምርኮ፥ ለብዝበዛና ለዕፍረት በአሕዛብ ነገሥታት እጅ ተጣልን፤ እስከ ዛሬም ድረስ በፊታችን እፍረት እንኖራለን።
“ነገር ግን ተመልሰው ዐመፁብህ፤ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፤ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ እጅግም አስቈጡህ።
ለዐመፀኞች ልጆች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር፤ ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ምክር ይመክራሉ፤ ኀጢአትንም በኀጢአት ላይ ይጨምሩ ዘንድ ከመንፈሴ ዘንድ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ።
እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፥ “ወደምልክህ ሁሉ ዘንድ ትሄዳለህና፥ የማዝዝህንም ሁሉ ትናገራለህና፦ ሕፃን ነኝ አትበል።
ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና በእፍረታችን ተኝተናል፤ ውርደታችንም ሸፍኖናል።”
“አንድ የመጽሐፍ ክርታስ ውሰድ፥ ለአንተም ከተናገርሁበት ቀን ከይሁዳ ንጉሥ ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት።
“እናንተና አባቶቻችሁ፥ ነገሥታቶቻችሁም፥ አለቆቻችሁም የምድርም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን እግዚአብሔር ያሰበው፥ በልቡም ያኖረው አይደለምን?
“በእግዚአብሔር ቤት በር ቁም፤ ይህንም ቃል እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ለእግዚአብሔር ትሰግዱ ዘንድ በእነዚህ በሮች የምትገቡ ከይሁዳ ያላችሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
“የሰው ልጅ ሆይ፥ ለአስቈጡኝ ለእስራኤል ቤት ይህ ትርጓሜ ምን እንደ ሆነ አታውቁምን? በላቸው። እንዲህም ብለህ ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ ንጉሥዋንና መኳንንቶችዋንም ማረከ፤ ወደ ሀገሩም ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።
ለዐመፀኛውም ቤት ምሳሌን ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣድ፥ ድስቲቱን ጣድ፥ ውኃም ጨምርባት።
ያም ሰው፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አሳይህ ዘንድ አንተ ወደዚህ መጥተሃልና በዐይንህ እይ፤ በጆሮህም ስማ፤ የማሳይህንም ሁሉ በልብህ ጠብቅ፤ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር” አለኝ።
ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል።
ሙሴና አሮንም ማኅበሩን በዐለቷ ፊት ሰብስበው፥ “እናንተ ዓመፀኞች፥ እንግዲህ ስሙ፤ በውኑ ከዚህች ዐለት ውኃን እናወጣላችሁ ነበር?” አሏቸው።
“እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ።
በራስህ የማልህላቸውን አገልጋዮችህን አብርሃምንና ይስሐቅን፥ ያዕቆብንም አስብ፤ የዚህን ሕዝብ ልበ ደንዳናነት፥ ክፋቱንም፥ ኀጢአቱንም አትመልከት፤