ሕዝቅኤል 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፈጽሞ ሳያዩ ከገዛ ልባቸው አንቅተው ትንቢት ለሚናገሩ ወዮላቸው! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ አንዳች ነገር ሳያዩ የራሳቸውን መንፈስ ለሚከተሉ ሞኞች ነቢያት ወዮላቸው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምንም ሳያዩ የገዛ መንፈሳቸውን የሚከተሉ ሞኞች ነቢያት ወዮላቸው! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ከአሳባቸው አፍልቀው ትንቢት ለሚናገሩና ራእይ ሳያዩ ‘ራእይ አይተናል’ ለሚሉ ለእነዚህ ለሞኞች ነቢያት ወዮላቸው! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምንምን ሳያዩ የገዛ መንፈሳቸውን ለሚከተሉ ለሰነፎች ነቢያት ወዮላቸው! |
ኀያል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትስሙ፤ ከንቱነትን ያስተምሩአችኋል፤ ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ ልባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ።
ስለ ነቢያት ልቤ በውስጤ ተሰብሮአል፤ አጥንቶችም ሁሉ ታውከዋል፤ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ፤ ከጌትነቱም ክብር የተነሣ እኔም በመከራ እንደ ተቀጠቀጠ ሰው፥ የወይን ጠጅ እንዳሸነፈውም እንደ ሰካራም ሰው ሆኛለሁ።
ነቢዩም ኤርምያስ ሐሰተኛውን ሐናንያን፥ “ሐናንያ ሆይ ስማ፤ እግዚአብሔር አልላከህም፤ ነገር ግን ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል።
ኖን። ነቢያትሽ ከንቱና ዕብደትን አይተውልሻል፤ ምርኮሽን ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፤ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።
እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስን ለማጥመድ ለእጅ ድጋፍ ሁሉ መከዳ ለሚሰፉ፥ ለሰውም ሁሉ ራስ እንደ እየቁመቱ ሽፋን ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤን ነፍስ ታጠምዳላችሁ፤ በውኑ እናንተ ነፍሳችሁን ታድናላችሁ?
“የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፤ እረኞችንም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች ራሳቸውን ያሰማራሉን? እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን?
የበቀል ወራት መጥቶአል፤ የፍዳም ወራት ደርሶአል፤ እስራኤልም እንደ አበደ ነቢይና ርኩስ መንፈስ እንደ አለበት ሰው ይታመማል፤ ከኀጢአትህና ከጠላትነትህ ብዛት የተነሣም ቍጣህን አበዛህ።
እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! የጽድቅንና የዕውቀትን መክፈቻ ወስዳችሁ ትሰውራላችሁና፤ እናንተም አትገቡምና፤ የሚገቡትንም መግባትን ትከለክሉአቸዋላችሁ።”
በትዕቢት ተነፍቶአል፤ አንዳችም አያውቅም፤ ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፤ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።