ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ አሉትም፥ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ማፈርን እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
ዘፀአት 9:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈርዖን ገብተህ እንዲህ በለው፦ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ በለው፤ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ “ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ግባ እንዲህም በለው የዕብራውያን አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ንጉሡ ሄደህ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል በለው፦ ‘ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ ወደ ፈርዖን ዘንድ ገብተህ ንገረው፤ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ። |
ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ አሉትም፥ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ማፈርን እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
እነርሱም ቃልህን ይሰማሉ፤ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ትገባላችሁ፦ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ጠርቶናል፤ አሁንም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንሠዋ ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ወደ ምድረ በዳ እንሄዳለን ትሉታላችሁ።
ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲህ አሉት፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል ያደርግልኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።’ ”
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ማልደህ ተነሣ፤ በፈርዖንም ፊት ቁም፤ እነሆ፥ እርሱ ወደ ውኃ ይወርዳል፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በምድረ በዳ እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ማልደህ ተነሣ፤ በፈርዖንም ፊት ቆመህ እንዲህ በለው፦ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ።