ዘፀአት 36:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምስቱንም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንዱን ከሌላው ጋር አጋጠሙ፤ አምስቱንም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው እንዲሁ አጋጠሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ በማጋጠም ሰፏቸው፤ የቀሩትን ዐምስቱንም እንዲሁ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምስቱን መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አጋጠመ፥ ሌሎቹንም አምስት መጋረጃዎች እንዲሁ እርስ በርሳቸው አጋጠመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱንም አምስቱን በአንድ በኩል፥ ሌሎቹንም አምስቱን በሌላ በኩል አገጣጥመው ሰፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምስቱንም መጋረጆች እርስ በርሳቸው አጋጠሙ፤ አምስቱንም መጋረጆች እንዲሁ እርስ በርሳቸው አጋጠሙ። |
በእግዚአብሔር ቤት፥ በአምላካችን ቤት አደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ።
አምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ፤ ሌሎችም አምስት መጋረጃዎች እንዲሁ እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ።።
ከሚጋጠሙትም መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አደረጉ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አደረጉ።
ወንድሞቻችን! አንድ ቃል እንድትናገሩ፥ እንዳታዝኑ፥ ፍጹማንም እንድትሆኑ፥ ሁላችሁንም፦ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እማልዳችኋለሁ፤ እንዳትለያዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆናችሁ ኑሩ።