እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፤ በዚያም ሁን፤ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ፥ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ፤ ሕግንም ትሠራላቸዋለህ” አለው።
ዘፀአት 34:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ሁለት የድንጋይ ጽላት እንደ ፊተኞቹ አድርገህ ቅረጽ፤ ወደ እኔም ወደ ተራራ ውጣ፤ በሰበርሃቸው በፊተኞቹ ጽላት የነበሩትን ቃላት እጽፍባቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤ “እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላት ጥረብ፤ እኔም አንተ በሰበርሃቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላት ላይ የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞቹ አድርገህ ጥረብ፥ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመጀመሪያዎቹን የሚመስሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ቅረጽ፤ እኔም አንተ በሰበርካቸው ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፍባቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞች አድርገህ ጥረብ፤ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፤ በዚያም ሁን፤ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ፥ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ፤ ሕግንም ትሠራላቸዋለህ” አለው።
እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ ሁለቱን የምስክር ጽላት፥ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።
እንዲህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ ጥጃውንም ዘፈኑንም አየ፤ የሙሴም ቍጣ ተቃጠለ፤ እነዚያንም ሁለቱን ጽላት ከእጁ ጥሎ ከተራራው በታች ሰበራቸው።
በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእግዚአብሔር ፊት ነበረ፤ እንጀራም አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም። በጽላቱም ዐሥሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።
ሙሴም እንደ ፊተኞቹ አድርጎ ሁለት የድንጋይ ጽላት ቀረጸ፤ ሁለቱንም የድንጋይ ጽላት በእጁ ወሰደ፤ በነጋውም ማልዶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤
ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ፤ ለኔርዩም ልጅ ለጸሓፊው ለባሮክ ሰጠው፤ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ጻፈበት፤ ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ቃል ብዙ ቃል ተጨመረበት።