Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 32:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ጽላቱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም በጽ​ላቱ ላይ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ባ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽሕ​ፈት ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ጽላቱ የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፤ በጽላቱ ላይ የተቀረጸ ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጽላቶቹ የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፥ በጽላቶቹ ላይ የተቀረው ጽሑፍም የእግዚአብሔር ጽሑፍ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እነዚህም ጽላቶች የእግዚአብሔር ሥራ ናቸው። በላያቸው ላይ ያሉት ጽሑፎች የተቀረጹት በእግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕፈቱም በጽላቶች ላይ የተቀረጸባቸው የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 32:16
12 Referencias Cruzadas  

ማን በብ​ረት ብር​ዕና በእ​ር​ሳስ፥ በዓ​ለት ላይ በቀ​ረ​ፀው!


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።


ሙሴም ተመ​ለሰ፤ ሁለ​ቱ​ንም የም​ስ​ክር ጽላት በእጁ ይዞ ከተ​ራ​ራው ወረደ፤ የድ​ን​ጋይ ጽላ​ቱም በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለት ወገን ተጽ​ፎ​ባ​ቸው ነበር።


ኢያ​ሱም ሲጮሁ የሕ​ዝ​ቡን ድምፅ ሰምቶ ሙሴን፥ “የሰ​ልፍ ድምፅ በሰ​ፈሩ ውስጥ አለ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት እንደ ፊተ​ኞቹ አድ​ር​ገህ ቅረጽ፤ ወደ እኔም ወደ ተራራ ውጣ፤ በሰ​በ​ር​ሃ​ቸው በፊ​ተ​ኞቹ ጽላት የነ​በ​ሩ​ትን ቃላት እጽ​ፍ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ሙሴም እንደ ፊተ​ኞቹ አድ​ርጎ ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ቀረጸ፤ ሁለ​ቱ​ንም የድ​ን​ጋይ ጽላት በእጁ ወሰደ፤ በነ​ጋ​ውም ማልዶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤


እና​ንተ ራሳ​ች​ሁም በእኛ የተ​ላ​ከች የክ​ር​ስ​ቶስ መል​እ​ክት እንደ ሆና​ችሁ ያው​ቃሉ፤ ይህ​ቺ​ውም የተ​ጻ​ፈች በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነው እንጂ በቀ​ለም አይ​ደ​ለም፤ በሥጋ ልብ ሠሌ​ዳ​ነት ነው እንጂ በድ​ን​ጋይ ሠሌ​ዳም አይ​ደ​ለም።


ስለ​ዚያ ስለ አለ​ፈው የፊቱ ብር​ሃን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሙ​ሴን ፊት መመ​ል​ከት እስ​ኪ​ሳ​ና​ቸው ድረስ በዚ​ያች በድ​ን​ጋይ ላይ በፊ​ደል ለተ​ቀ​ረ​ጸች ለሞት መል​እ​ክት ክብር ከተ​ደ​ረ​ገ​ላት፥


“በዚ​ያን ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ፊተ​ኞች ያሉ​ትን ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ለአ​ንተ ቀር​ፀህ ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ ለአ​ን​ተም የእ​ን​ጨት ታቦት ሥራ፤


እኔም ተመ​ልሼ ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ሁለ​ቱም የቃል ኪዳን ጽላት በሁ​ለቱ እጆች ነበሩ።


ከእ​ነ​ዚያ ዘመ​ናት በኋላ ለቤተ እስ​ራ​ኤል የም​ገ​ባው ቃል ይህ ነው፦ ሕጌን በል​ባ​ቸው አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ በሕ​ሊ​ና​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos