በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
ዘፀአት 33:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን፣ ማንም እኔን አይቶ መኖር ስለማይችል፣ ፊቴን ማየት አትችልም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም “ሰው አይቶኝ መኖር አይችልምና ፊቴን ማየት አትችልም” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፊቴን አይቶ ለመኖር የሚችል ሰው ስለሌለ ፊቴን ለማየት አትችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም፦ ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም አለ። |
በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርም የቆመበትን ቦታ አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚያበራ፥ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።
ደግሞም፥ “እኔ የአባቶችህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቶአልና ፊቱን መለሰ።
እስከ አልፍም ድረስ እጄን በላይህ እጋርዳለሁ፤ እጄንም ፈቀቅ አደርጋለሁ፤ በዚያ ጊዜ ጀርባዬን ታያለህ፤ ፊቴ ግን ለአንተ አይታይም።”
እኔም፥ “ከንፈሮች የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዐይኖች የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!” አልሁ።
አላችሁም፦ እነሆ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፤ ከእሳቱም መካከል ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰው ጋር ሲነጋገር፥ ሰውዬው በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል።
እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።
ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ ዐወቀ። ጌዴዎንም፥ “አቤቱ! አምላኬ ሆይ! ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና” አለ።