ዘፀአት 32:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮን የሠራውን ጥጃ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር ሕዝቡን ቀሠፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮን በሠራው ጥጃ ባደረጉት ነገር እግዚአብሔር ሕዝቡን በመቅሠፍት መታ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮን የሠራውን ጥጃ ስለ ሠሩ ጌታ ሕዝቡን ቀሠፈ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወርቅ ጥጃ ምስል እንዲሠራላቸው አሮንን በማስገደዳቸው እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ከባድ በሽታ ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮን የሠራውን ጥጃ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር ሕዝቡን ቀሠፈ። |
ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፤ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፥ “እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው” አላቸው።
ከዚህም በኋላ ይህ ሰው በዐመፅ ዋጋዉ መሬት ገዛ፤ በምድር ላይም በግንባሩ ወደቀና ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ።