እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድርጌልሃለሁ፤ እነሆም፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ፥ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።
ዘፀአት 31:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እነሆ፥ ከዳን ነገድ የሚሆን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ሰጠሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ዕውቅትን ሰጠሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተጨማሪም ከዳን ነገድ የሆነውን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን እንዲረዳው መርጬዋለሁ። “እንዲሁም ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ ለእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ብልኀትን ሰጥቻቸዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም እነሆ ከእርሱ ጋር ከዳን ነገድ የሆነውን የአሒሳማክን ልጅ ኤልያብን ሰጥቼዋለሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ እንዲያደርጉ በልባቸው ጥበበኞች በሆኑት ሁሉ ላይ ጥበብን አኑሬአለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱም ጋር እንዲሠራ ከዳን ነገድ የአሒሳማክን ልጅ ኦሆሊአብን መርጬአለሁ፤ እኔ ያዘዝኩህን ነገር ሁሉ እንዲሠሩ ሌሎችም የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ታላቅ ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጌአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም እነሆ ከእርሱ ጋር ከዳን ነገድ የሚሆን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ሰጠሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በልባቸው ጥበበኞች በሆኑት ሁሉ ጥበብን አኖርሁ። |
እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድርጌልሃለሁ፤ እነሆም፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ፥ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።
አንተም የጥበብ መንፈስ ለሞላሁባቸው፥ በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ተናገር። እነርሱም ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ ለአሮን ለቤተ መቅደስ የሚሆን የተለየ ልብስ ይሥሩ፤
በአንጥረኛ፥ በብልህ ሠራተኛም፥ በሰማያዊና በሐምራዊ፥ በቀይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍታም በሚሠራ ጠላፊ፥ በሸማኔም ሥራ የሚሠራውን፥ ማናቸውንም ሥራና በብልሃት የሚሠራውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በእነርሱ ልብ ጥበብን ሞላ።
በእነርሱም ዘንድ ያሉት፥ ሥራ ሲሠሩ የነበሩት በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ ድንኳኑን ከዐሥር መጋረጃዎች ሠሩ፤ እነርሱንም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊም፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ሠሩ፤ በእነርሱም ላይ በጥልፍ ሥራ ኪሩቤልን አደረጉባቸው።
ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነ የአሒሳሚክ ልጅ ኤልያብ ነበረ፤ እርሱም በሰማያዊ፥ በሐምራዊ፥ በቀይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍታ የሽመና ሥራ ይሠራ ዘንድ የቅርጽ፥ የሽመናና የጥልፍ ሥራ አለቃ ነበረ።
እነዚህ አሮንና ሙሴ እግዚአብሔር፥ “ከግብፅ ምድር ከሠራዊቶቻቸው ጋር የእስራኤልን ልጆች አውጡ” ያላቸው ናቸው።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ሌሎች ሰባ ሰዎችን መረጠ፤ ሁለት ሁለት አድርጎም ሊሄድበት ወደ አለው ከተማና መንደር በፊቱ ላካቸው።
የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ፥ ሲጾሙም መንፈስ ቅዱስ፥ “በርናባስንና ሳውልን እኔ ለፈለግኋቸው ሥራ ለዩልኝ” አላቸው።