Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 31:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እኔም እነሆ ከእርሱ ጋር ከዳን ነገድ የሆነውን የአሒሳማክን ልጅ ኤልያብን ሰጥቼዋለሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ እንዲያደርጉ በልባቸው ጥበበኞች በሆኑት ሁሉ ላይ ጥበብን አኑሬአለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በተጨማሪም ከዳን ነገድ የሆነውን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን እንዲረዳው መርጬዋለሁ። “እንዲሁም ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ ለእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ብልኀትን ሰጥቻቸዋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከእርሱም ጋር እንዲሠራ ከዳን ነገድ የአሒሳማክን ልጅ ኦሆሊአብን መርጬአለሁ፤ እኔ ያዘዝኩህን ነገር ሁሉ እንዲሠሩ ሌሎችም የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ታላቅ ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጌአለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እኔም እነሆ፥ ከዳን ነገድ የሚ​ሆን የአ​ሂ​ሳ​ሚ​ክን ልጅ ኤል​ያ​ብን ሰጠሁ፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ለሆ​ኑት ሁሉ ዕው​ቅ​ትን ሰጠሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እኔም እነሆ ከእርሱ ጋር ከዳን ነገድ የሚሆን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ሰጠሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በልባቸው ጥበበኞች በሆኑት ሁሉ ጥበብን አኖርሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 31:6
26 Referencias Cruzadas  

እርሱና የዳን ነገድ የሆነው የአሒሳማክ ልጅ ኤልያብ እንዲያስተምሩ በልባቸው አሳደረባቸው።


“በእናንተ መካከል ያሉ በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ መጥተው ጌታ ያዘዘውን ሁሉ ያድርጉ።


ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ የተለየ እንዲሆን ለአሮን ልብስ እንዲሠሩለት የጥበብ መንፈስ ለሞላሁባቸው በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ተናገር።


እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ “በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ፤” አለ።


ከዚህም በኋላ ጌታ ሌሎች ሰባ ሁለት ሰዎችን መረጠ፤ ሁለት ሁለትም አድርጎ ራሱ ሊሄድበት ወደአሰበው ከተማና ስፍራ ሁሉ አስቀድሞ ላካቸው።


እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደፊትም ሊያገኘው ከሚችለው የበለጠ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ።


ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።


ሥራ ሲሠሩ ከነበሩት ጥበበኞች የሆኑት ሁሉ ማደሪያውን ሠሩ፤ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ፥ ኪሩቤልም የተጠለፈባቸው ዐሥር መጋረጃዎች ሠሩ።


እነዚህ አሮንና ሙሴ ጌታ፦ “የእስራኤልን ልጆች በየነገዳቸው ከግብጽ ምድር አውጡ” ያላቸው ናቸው።


ለፈርጥ የሚሆነውን ድንጋይ እንዲቀርጽ፥ እንጨት እንዲጠርብ፥ ሁሉንም ሥራ እንዲሠራ ሞላሁበት።


በአንጥረኝነት፥ በንድፍ፥ በሰማያዊ፥ በሐምራዊ፥ በቀይ ግምጃና በጥሩ በፍታ በመጥለፍ፥ ሸማኔ በሚሠራው ሥራ፥ በማናቸውንም ሥራና በብልሃት የሚሠራውን ሁሉ እንዲያደርጉ በእነርሱ ልብ ጥበብን ሞላ።”


ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሒሳማክ ልጅ ኤልያብ ነበረ፤ እርሱም ቀራጭ፥ ንድፍ አውጪ፥ እንዲሁም በሰማያዊ በሐምራዊ፥ በቀይ ግምጃና በጥሩ በፍታ የሚጠልፍ ነበረ።


ሙሴ ለእስራኤል ልጆች ማህበር ሁሉ እንዲህ አለ፦ “ጌታ ያዘዘው ነገር ይህ ነው፥ እንዲህ በማለት፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios