የውስጠኛውንም አደባባይ ቅጥር ሦስቱን ተራ በተጠረበ ድንጋይ፥ አንዱንም ተራ በዝግባ ሣንቃ ሠራው፤ በመቅደሱ ፊት ለፊት ላለው ቤት ወለልም መጋረጃ ሠራ።
ዘፀአት 27:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለድንኳኑም አደባባይ ሥራ፤ ከጥሩ በፍታ የተሠሩ የአደባባዩ መጋረጃዎችም በደቡብ በኩል ይሁኑ። የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ አብጅለት፤ በደቡብ በኩል ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ይሁን፤ ከቀጭን በፍታ የተፈተሉ መጋረጃዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የማደሪያውን አደባባይ ሥራ፤ በደቡብ በኩል ከጥሩ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ይሁኑ፥ የአንዱ ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለድንኳኑ አደባባይ ክልል መጋረጃዎች ከቀጭን ሐር ሥራ፤ የመጋረጃዎቹም ርዝመት ከደቡብ በኩል አርባ አራት ሜትር ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማደሪያውንም አደባባይ ሥራ፤ በደቡብ ወገን የጥሩ በፍታ መጋረጆች ይሁኑለት፥ የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤ |
የውስጠኛውንም አደባባይ ቅጥር ሦስቱን ተራ በተጠረበ ድንጋይ፥ አንዱንም ተራ በዝግባ ሣንቃ ሠራው፤ በመቅደሱ ፊት ለፊት ላለው ቤት ወለልም መጋረጃ ሠራ።
በእግዚአብሔር ፊት ያለው የናሱ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የሰላሙንም መሥዋዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሰላሙንም መሥዋዕት ስብ አሳርጎአልና በእግዚአብሔር ቤት ፊት የነበረውን የአደባባዩን መካከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ።
ከተጋጠሙትም መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ጠርዝ ላይ አምሳ ቀለበቶችን አደረጉ፤ እንዲሁም በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዝ በሚጋጠሙበት በኩል አምሳ ቀለበቶችን አደረጉ።
የአደባባዩንም መጋረጆች፥ ምሰሶዎቹንም፥ እግሮቹንም፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ፥ አውታሮቹንም፥ ካስማዎቹንም፥ ለምስክሩ ድንኳን ማገልገያ የሚሆኑትን ዕቃዎች ሁሉ፤
በድንኳኑና በመሠዊያውም ዙሪያ አደባባዩን ሠራ፤ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ ዘረጋ። እንዲሁም ሙሴ ሥራውን ፈጸመ።
ወደ ውስጠኛው አደባባይም አገባኝ፤ እነሆም በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፤ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።
በውስጠኛውም አደባባይ በሰሜኑና በምሥራቁ በኩል በሌላው በር አንጻር በር ነበረ፤ ከበርም እስከ በር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።
ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አገባኝ፤ እነሆም ሁለት ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፤ መግቢያውም ወደ ደቡብ ይመለከት ነበረ፤ ሌላውም ወደ ደቡብ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፤ መግቢያውም ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።
በውስጠኛውም አደባባይ በሃያው ክንድ አንጻር፥ በውጭውም አደባባይ በወለሉ አንጻር በሦስት ደርብ በትይዩ የተሠራ መተላለፊያ ነበረ።
በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ያለውን የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፥ ለማገልገልም የሚሠሩበትን ዕቃ ሁሉ ይሸከሙ፤ በዚህም ያገልግሉ።
በዙሪያውም የሚቆሙት የአደባባዩ ምሰሶዎች፥ እግሮቹም፥ የአደባባዩ ደጃፍ መጋረጃ ምሰሶዎች፥ እግሮቻቸውም፥ ካስማዎቹም፥ አውታሮቹም፥ ዕቃዎቹና ማገልገያዎቹ ሸክማቸው ነው፤ የሚጠብቁትንም የሸክማቸውን ዕቃ ሁሉ በየስማቸው ቍጠሩ።