ዘፀአት 25:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገበታም ላይ ኅብስተ ገጹን ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማንኛውም ጊዜ በፊቴ እንዲሆን በገጸ ኅብስቱ በዚህ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገበታው ላይ ኅብስተ ገጹን ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠረጴዛውም በታቦቱ ፊት ለፊት ይቀመጥ፤ ለእኔ የሚቀርበው የተቀደሰ ኅብስት ዘወትር በጠረጴዛው ላይ መኖር አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገበታም ላይ የገጽ ኅብስት ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ። |
ደግሞም ገጸ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም ለእህል ቍርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በልክ ሁሉ ያገለግሉ ዘንድ ሹሞአቸው ነበር።
በየጥዋቱና በየማታውም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የገጹንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል።
ሰሎሞንም እንዲህ ሲል ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ላከ፥ “ከአባቴ ከዳዊት ጋር እንዳደረግህ፥ የሚቀመጥበትንም ቤት ይሠራ ዘንድ የዝግባ እንጨት እንደ ላክህለት፥ እንዲሁ ለእኔ አድርግ።
እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን ለማጠን፥ የገጹንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በአምላካችንም በእግዚአብሔር በዓላት ለማቅረብ እኔ ልጁ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራለሁ፤ እርሱንም እቀድሳለሁ።
መሠዊያውም ቁመቱ ሦስት ክንድ፥ ርዝመቱ ሁለት ክንድ፥ ወርዱም ሁለት ክንድ ሆኖ ከእንጨት ተሠርቶ ነበር፤ ማዕዘኖቹም፥ እግሩም፥ አገዳዎቹም ከእንጨት ተሠርተው ነበር፤ እርሱም፥ “በእግዚአብሔር ፊት ያለችው ገበታ ይህች ናት” አለኝ።
በመሠዊያዬ ላይ ርኩስ እንጀራ ታቀርባላችሁ። እናንተም፦ ያረከስንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። የእግዚአብሔር ገበታ የተነቀፈ ነው በማለታችሁ ነው።
በኅብስተ ገጹ ገበታ ላይም ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ጭልፋዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለማፍሰስም መቅጃዎቹን ያድርጉበት፤ ሁልጊዜም የሚኖር ኅብስት በእርሱ ላይ ይሁን።
የመጀመሪያዪቱም ድንኳን ተዘጋጅታ ነበርና፥ በእርስዋም ቅድስት በምትባለው ውስጥ መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት ነበረባት።
ካህኑም ለዳዊት መልሶ፥ “ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፤ ነገር ግን የተቀደሰ እንጀራ አለ፤ ብላቴኖቹ ከሴቶች ንጹሓን እንደ ሆኑ መብላት ይችላሉ” አለው።
ዳዊትም ለካህኑ መልሶ፥ “ከሴቶች ተለይተን ወደ መንገድ ከወጣን ዛሬ ሦስተኛ ቀናችን ነው። እኔም ብላቴኖቼም ንጹሓን ነን። ነገር ግን ዛሬ ሰውነቴ ንጽሕት ስለ ሆነች ነው እንጂ ይህች መንገድ የነጻች አይደለችም” አለው።
ካህኑ አቤሜሌክም በእርሱ ፋንታ ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ከአለው ኅብስት በቀር ሌላ እንጀራ አልነበረምና የቍርባኑን ኅብስት ሰጠው።