ሚክያስም አለ፥ “እንዲህ አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሰማሁት እኔ አይደለሁምን? እንዲህ አይደለም፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።
ዘፀአት 24:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም፥ አሮንም፥ ናዳብም፥ አብዩድም፥ ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴና አሮን፣ ናዳብና አብዩድ እንደዚሁም ሰባዎቹ የእስራኤል አለቆች ወደ ተራራው ወጡ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴ፥ አሮን፥ ናዳብ፥ አቢሁና ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወጡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ፥ አሮን፥ ናዳብ፥ አቢሁና ከእስራኤልም መሪዎች ሰባዎቹ ወደ ተራራው ወጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም አሮንም ናዳብም አብዩድም ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወጡ፤ |
ሚክያስም አለ፥ “እንዲህ አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሰማሁት እኔ አይደለሁምን? እንዲህ አይደለም፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።
እግዚአብሔርም፥ “ሂድ፤ ውረድ፤ አንተ አሮንም ከአንተ ጋር ትወጣላችሁ፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን እግዚአብሔር እንዳያጠፋቸው ወደ እግዚአብሔር ይወጡ ዘንድ አይደፋፈሩ” አለው።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አንተ፥ አሮንም፥ ናዳብም፥ አብዩድም፥ ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወደ እግዚአብሔር ውጡ፤ በሩቁም ለእግዚአብሔር ስገዱ፤
“አንተም ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አብዩድንም፥ አልዓዛርንም ኢታምርንም አቅርብ።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረዥምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ ምስጋናውም ቤቱን ሞልቶት ነበር።
አለቃው ግን እርሱ በእግዚአብሔር ፊት እንጀራ ይበላ ዘንድ ይቀመጥባታል፤ በበሩ ይገባል፤ በዚያም መንገድ ይወጣል።”
የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፤ በላዩም ዕጣን ጨመሩበት፤ በእግዚአብሔርም ፊት እግዚአብሔር ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች፥ ለሕዝቡ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ይሆኑ ዘንድ የምታውቃቸውን፥ ሰባ ሰዎች ሰብስብልኝ፤ ወደ ምስክሩም ድንኳን አምጣቸው፤ በዚያም ከአንተ ጋር አቁማቸው።