Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 19:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሂድ፤ ውረድ፤ አንተ አሮ​ንም ከአ​ንተ ጋር ትወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ካህ​ና​ቱና ሕዝቡ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወጡ ዘንድ አይ​ደ​ፋ​ፈሩ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ውረድና አሮንን ከአንተ ጋራ ይዘኸው ውጣ፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን ወደ እግዚአብሔር ለመምጣት መጣደፍ የለባቸውም፤ አለዚያ እርሱ ቍጣውን ያወርድባቸዋል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ጌታም፦ “ሂድ፥ ውረድ፤ አሮንንም ከአንተ ጋር ይዘህ ና፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን እንዳያጠፋቸው ወደ ጌታ ለመውጣት አይተላለፉ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እግዚአብሔርም “ውረድና አሮንን ይዘህ ና፤ ካህናቱም ሆኑ ሕዝቡ ወደ እኔ ለመውጣት ወሰኑን ማለፍ የለባቸውም፤ ይህን ቢያደርጉ ግን እኔ እግዚአብሔር እቀጣቸዋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እግዚአብሔርም፦ ሂድ፥ ውረድ፤ አንተ አሮንም ከአንተ ጋር ትወጣላችሁ፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን እግዚአብሔር እንዳያጠፋቸው ወደ እግዚአብሔር ይወጡ ዘንድ አይተላለፉ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 19:24
20 Referencias Cruzadas  

እን​ግ​ዲህ ምሕ​ረ​ትን እን​ድ​ን​ቀ​በል፥ በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንም ጊዜ የሚ​ረ​ዳ​ንን ጸጋ እን​ድ​ና​ገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእ​ም​ነት እን​ቅ​ረብ።


አም​ላ​ካ​ችን በእ​ው​ነት የሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነውና።


ነገር ግን ተስፋ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን ይሆን ዘንድ፥ ያመ​ኑ​ትም ያገ​ኙት ዘንድ፥ መጽ​ሐፍ ሁሉን በኀ​ጢ​አት ዘግ​ቶ​ታል።


ታዲያ ኦሪት ለምን ተሠ​ራች? ኦሪ​ትስ ኀጢ​አ​ትን ታበ​ዛት ዘንድ፥ ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለት ያ ዘር እስ​ኪ​መጣ ድረስ፥ በመ​ላ​እ​ክት በኩል በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው እጅ ወረ​ደች።


የኦ​ሪት ሕግ በአ​ፍ​ራሹ ላይ ቅጣ​ትን ያመ​ጣ​ልና፤ የኦ​ሪት ሕግም ከሌለ መተ​ላ​ለፍ የለም።


ኦሪት በሙሴ ተሰ​ጥ​ታን ነበ​ርና፤ ጸጋና እው​ነት ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆነ​ልን።


“ኦሪ​ትም ነቢ​ያ​ትም ከጥ​ንት ጀምሮ እስከ ዮሐ​ንስ ድረስ ነበሩ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ይሰ​በ​ካል፤ ሁሉም ወደ እር​ስዋ ይጋ​ፋል።


“ወደ ጠባቡ በር ትገቡ ዘንድ በርቱ፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሊገቡ የሚሹ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ግን አይ​ች​ሉም።


ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፤ ግፈኞችም ይናጠቋታል።


ሙሴም፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወጡ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አንተ፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ውጡ፤ በሩ​ቁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስገዱ፤


ለሕ​ዝ​ቡም በዙ​ሪ​ያው ወሰን አድ​ር​ግ​ላ​ቸው፤ ወደ ተራ​ራው እን​ዳ​ት​ወጡ፥ ከእ​ርሱ ማን​ኛ​ው​ንም ክፍል እን​ዳ​ት​ነኩ ተጠ​ን​ቀቁ፤ ተራ​ራ​ው​ንም የነካ ፈጽሞ ይሞ​ታል” ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤


ሙሴም ወደ ሕዝቡ ወረደ፤ ይህ​ንም ነገ​ራ​ቸው።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ እኔ በሚ​ቀ​ርቡ እመ​ሰ​ገ​ና​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት እከ​ብ​ራ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው” አለው፤ አሮ​ንም ደነ​ገጠ።


ወደ አው​ድማ ዳርም በደ​ረሱ ጊዜ ላሞቹ ሰረ​ገ​ላ​ውን ሲስቡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ዘን​በል ብላ​ለ​ችና ታቦ​ቷን ሊይዝ ዖዛ እጁን ዘረጋ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios