La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 23:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“የጠ​ላ​ት​ህን በሬ ወይም አህ​ያ​ውን ጠፍቶ ብታ​ገ​ኘው ፈጽሞ መል​ስ​ለት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“የጠላትህ በሬ ወይም አህያ ሲባዝን ብታገኘው ወደ እርሱ መልሰው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጠላትህን በሬ ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኘው ለእርሱ መልስለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የጠላትህ በሬ ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኝ መልስለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የጠላትህን በሬ ወይም አህያውን ጠፍቶ ብታገኘው በፍጹም መልስለት።

Ver Capítulo



ዘፀአት 23:4
9 Referencias Cruzadas  

ወይም የጠ​ፋ​ውን ነገር ቢያ​ገኝ፥ ስለ​ዚ​ህም ቢዋሽ፥ ሰው ኀጢ​አ​ትን ለመ​ሥ​ራት ከሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች ሁሉ በአ​ን​ዲቱ በሐ​ሰት ቢምል፥


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።


ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።