ዘፀአት 22:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ‘ይህ የእኔ ነው’ ቢል፥ ክርክራቸው በፈጣሪ ፊት ይቅረብ፤ በፈጣሪ ፊት የተፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ ይክፈል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው በሬን፣ አህያን፣ በግን፣ ልብስን ወይም ማንኛውንም ንብረት ያለ አግባብ በባለቤትነት ይዞ ሳለ፣ ‘የእኔ ነው’ ባይ ቢመጣና ክርክር ቢነሣ፣ ባለጕዳዮቹ ነገሩን ለዳኞች ያቅርቡት፤ ዳኞቹ ጥፋተኛ ነው ያሉትም ለጎረቤቱ ዕጥፉን ይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰው ለባልንጀራው አህያ ወይም በሬ ወይም በግ ወይም ሌላ እንስሳ እንዲጠብቅለት በአደራ ቢሰጥ፥ ማንም ሳያይ ቢሞት ወይም ቢጎዳ ወይም ቢማረክ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለ ከብት፥ ስለ አህያ፥ ስለ በግ ስለ ልብስና ወይም ስለ ማንኛውም የጠፋ ዕቃ ሁለት ሰዎች ቢካሰሱ፥ ስለ ንብረቱ ባለቤትነት የተጣሉት ሁለቱ ሰዎች የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሆኑ ዳኞች ፊት ይቅረቡ፤ እግዚአብሔር በደሉን በዳኞቹ አማካይነት የሚገለጥበት ሰው፥ ለተበደለው ሰው ዕጥፍ አድርጎ ይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለ ሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ይህ የእኔ ነው ቢል፥ ክርክራቸው ወደ ፈራጆች ይድረስ፤ ፈራጆቹም የፈረዱበት እርሱ ለባልንጀራው በአንድ ሁሉት ይክፈል። |
በከተሞቻቸውም ከተቀመጡት ከወንድሞቻችሁ በደምና በደም መካከል፥ በሕግና በትእዛዝ፥ በሥርዐትና በፍርድም መካከል ያለ ማናቸውም ሰው ለፍርድ ወደ እናንተ ቢመጣ እግዚአብሔርን እንዳይበድሉ፥ ቍጣም በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳይመጣ አስጠንቅቁአቸው፤ እንዲህም ብታደርጉ በደለኞች አትሆኑም።
“ሰው በባልንጀራው ዘንድ አህያ ወይም በሬ ወይም በግ ወይም ሌላ እንስሳ እንዲጠብቅለት አደራ ቢያኖር፥ ማንም ሳያይ ቢሞት ወይም ቢጐዳ ወይም ቢማረክ፥
ወይም በሐሰት የማለበትን ነገር ቢመልስ፥ በሙሉ ይመልስ፤ ከዚያም በላይ አምስተኛውን ክፍል ጨምሮ የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን ለባለ ገንዘቡ ይስጠው።