ዘፀአት 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌባው ባይገኝ ባለቤቱ ወደ ፈጣሪ ፊት ይቅረብ፤ ባልንጀራው አደራ በአስቀመጠበት ገንዘብም ላይ እንዳልተተነኰለና ክፉ እንዳላሰበ ይማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌባው ካልተያዘ ግን፣ የቤቱ ባለቤት በንብረቱ ስርቆት ላይ እጁ ይኑርበት ወይም አይኑርበት ይታወቅ ዘንድ ዳኞች ፊት ይቅረብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለ ሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ይህ የእኔ ነው ቢል ክርክራቸው ወደ እግዚአብሔር ይምጣ፤ እግዚአብሔርም የፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ አድርጎ ይክፈል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌባው ካልተገኘ ግን ዕቃውን በዐደራ የተቀበለው ሰው የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሆኑ ዳኞች ፊት ቀርቦ የዚያን ሰው ንብረት አለመስረቁን በመሐላ ያረጋግጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌባውም ባይገኝ ባለቤቱ ወደ ፈራጆች ይቅረብ፥ እጁንም በባልንጀራው ከብት ላይ እንዳልዘረጋ ይማል። |
ከእነዚህም ውስጥ የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ የሚያሠሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድስቱ ሺህም ጻፎችና ፈራጆች ነበሩ።
ጌታው ወደ ቤተ እግዚአብሔር ፈራጆች ይውሰደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃኑም አቅርቦ አፍንጫውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘለዓለምም ባሪያው ይሁነው።
ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ‘ይህ የእኔ ነው’ ቢል፥ ክርክራቸው በፈጣሪ ፊት ይቅረብ፤ በፈጣሪ ፊት የተፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ ይክፈል።
“አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በሀገርህ ደጅ ሁሉ በየነገዶችህ ፈራጆችንና መባውን የሚጽፉትን ሹሙ፤ ለሕዝቡም ቅን ፍርድን ይፍረዱ።