ዘፀአት 22:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰረቀው ደኅና ሆኖ በእጁ ቢገኝ፥ በሬ ወይም በግ ቢሆን፥ የሰረቀውን ያህል ሁለት እጥፍ ይክፈል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰረቀው እንስሳ በሬ ወይም አህያ ወይም በግ ከነሕይወቱ በእጁ ከተያዘ ዕጥፍ መክፈል አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰው በእርሻ ወይም በወይን ስፍራ ከብቱን ቢያሰማራ፥ የሌላውንም ሰው እርሻ ቢያስበላ፥ ከተመረጠ እርሻውና መልካም ከሆንው ወይኑ ይካስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰረቀው እንስሳ ላምም ቢሆን፥ አህያም ቢሆን፥ ወይም በግ ቢሆንና በሕይወት ቢገኝ ለያንዳንዱ ዕጥፍ ዋጋ ይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰረቀው ደኅና ሆኖ በእጁ ቢገኝ፥ በሬም ወይም አህያ ወይም በግ ቢሆን፥ የሰረቀውን ያህል ሁለት እጥፍ ይክፈል። |
“ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በአንድ በሬ ፋንታ አምስት በሬዎች፥ በአንድ በግም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል።
“የሰውን አዝመራ ከብቱን ያስበላ፥ የሌላ ሰው ወይንንም ያስበላ ሰው ቢኖር ግምቱን ይክፈል። የሰውን አዝመራ ፈጽሞ ቢያስበላ ግን በአጠገቡ ባለ አዝመራ ልክ ይክፈል፤ ወይንም ቢሆን በአጠገቡ ባለ ወይን ልክ ይክፈል።
“ሰው በባልንጀራው ዘንድ ብር ወይም ሌላ ዕቃ እንዲጠብቅለት አደራ ቢያኖር ከቤቱም ቢሰረቅ፥ ሌባው ቢገኝ እጥፍ ይክፈል።
ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ‘ይህ የእኔ ነው’ ቢል፥ ክርክራቸው በፈጣሪ ፊት ይቅረብ፤ በፈጣሪ ፊት የተፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ ይክፈል።
ካህናት ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ወደ ልቧ የሚገባ ነገርን ተናገሩ፤ ውርደቷ እንደ ተፈጸመ፥ ኀጢአቷም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች አጽናኑአት።
ምድሬንም በተጠሉ በጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኀጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”
ወይም በሐሰት የማለበትን ነገር ቢመልስ፥ በሙሉ ይመልስ፤ ከዚያም በላይ አምስተኛውን ክፍል ጨምሮ የበደሉን መሥዋዕት በሚያቀርብበት ቀን ለባለ ገንዘቡ ይስጠው።
ሳሙኤልም፥ “በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ ዛሬ በዚህች ቀን እግዚአብሔር ምስክር ነው፤ እርሱ የቀባውም ምስክር ነው” አላቸው፤ እነርሱም፥ “አዎ ምስክር ነው” አሉ።