ወደ ሲናም ተራራ ወረድህ፤ ከሰማይም ተናገርሃቸው፤ ቅኑን ፍርድና እውነቱን ሕግ፥ መልካሙንም ሥርዐትና ትእዛዝ ሰጠሃቸው፤
ዘፀአት 20:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እነዚህን ቃሎች ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም እነዚህን ቃሎች ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ለሕዝቡ ተናገረ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ |
ወደ ሲናም ተራራ ወረድህ፤ ከሰማይም ተናገርሃቸው፤ ቅኑን ፍርድና እውነቱን ሕግ፥ መልካሙንም ሥርዐትና ትእዛዝ ሰጠሃቸው፤
በምድረ በዳ በማኅበሩ መካከል የነበረ እርሱ ነው፤ በደብረ ሲና ከአነጋገረው መልአክና፤ ከአባቶቻችንም ጋር ለእኛ ሊሰጠን የሕይወትን ቃል የተቀበለ እርሱ ነው።
እግዚአብሔርም በተራራው ላይ በእሳት መካከል የተናገራችሁን ዐሠርቱን ቃላት ቀድሞ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቱ ላይ ጻፈ፤ እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ።
አንተ ከእሳት መካከል ሆኖ ሲናገር የሕያው እግዚአብሔርን ድምፅ እንደ ሰማህና በሕይወት እንዳለህ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ እንደ ሆነ፥
“እግዚአብሔር በተራራው ላይ፤ በእሳትና በጨለማ፥ በጭጋግና በዓውሎ ነፋስ መካከል ሆኖ በታላቅ ድምፅ እነዚህን ቃሎች ለጉባኤያችሁ ሁሉ ተናገረ፤ ምንም አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላት ላይ ጻፋቸው፤ ለእኔም ሰጣቸው።