ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፤ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ ለልጅ ልጃችሁም ሥርዐት ሆኖ ለዘለዓለም ታደርጉታላችሁ።
ዘፀአት 13:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቀን ወደ ቀን በየጊዜው ይህን ሕግ ጠብቁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ሥርዐት በተወሰነው ጊዜ በየዓመቱ ጠብቁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተወሰነለት ጊዜ ከዓመት ወደ ዓመት ይህችን ሥርዓት ጠብቃት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ይህን በዓል በየዓመቱ በተመደበለት ጊዜ የማክበር ሥርዓት ይሁንላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓመት በዓመት በወራቱ ይህችን ሥርዓት ጠብቃት። |
ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፤ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ ለልጅ ልጃችሁም ሥርዐት ሆኖ ለዘለዓለም ታደርጉታላችሁ።
በዚህም ቀን ሠራዊታችሁን ከግብፅ ሀገር አወጣዋለሁና ይህን ትእዛዝ ጠብቁት፤ እንግዲህ ይህን ቀን ለልጅ ልጃችሁ ለዘለዓለም ሥርዐት አድርጋችሁ ትጠብቃላችሁ።
ይህች ሌሊት ከግብፅ ምድር ስላወጣቸው ለእግዚአብሔር የተጠበቀች ናት፤ ይህች ሌሊት በእስራኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ እስከ ልጅ ልጃቸው ድረስ ለእግዚአብሔር የተጠበቀች ናት።
እግዚአብሔርም ለእናንተ ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ወደማለላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር፥ ወደ ከናኔዎናውያን፥ ወደ ኬጢዎናውያንም፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያን፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም ምድር በአገባችሁ ጊዜ ይህችን ሥርዐት በዚህ ወር አድርጉ።
የቂጣውን በዓል ጠብቁ፤ በአዲስ ወር ከግብፅ ምድር ወጥታችኋልና በዚህ ወር እንዳዘዝኋችሁ ሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ።