ዘፀአት 12:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስን ሰጠ፤ እነርሱም አዋሱአቸው። እነርሱም ግብፃውያንን በዘበዙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በግብጻውያን ፊት ለእስራኤላውያን ሞገስ ስለ ሰጣቸው፣ የጠየቋቸውን ሁሉ ሰጧቸው፤ ስለዚህ የግብጻውያንን ንብረት በዝብዘው ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት ሞገስን ሰጣቸው እነርሱም የፈለጉትን ሰጡአቸው። እነርሱም ግብጽን በዘበዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በግብጻውያን ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙና የጠየቁትንም ሁሉ ማግኘት እንዲችሉ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን የግብጽን ሀብት በዝብዘው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት የፈለጉትን እንዲሰጡአቸው ሞገስን ሰጠ። እነርሱም ግብፃውያንን በዘበዙ። |
በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በገንዘቦችና በእንስሶች፥ በሌላም ስጦታ ይረዷቸው ነበር።
እግዚአብሔርም በግብፃውያን ፊት ለሕዝቡ ሞገስን ሰጠ፤ አዋሱአቸውም፤ ይህ ሙሴም በግብፃውያንና በፈርዖን፥ በሹሞቹም ፊት እጅግ የከበረ ሰው ነበረ።
እግዚአብሔርንም ያመሰግኑ ነበር፤ በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ መወደድ ነበራቸው፤ እግዚአብሔርም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።
ከመከራውም ሁሉ አዳነው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።