Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 39:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዮ​ሴፍ ጋር ነበረ፤ ምሕ​ረ​ት​ንም አበ​ዛ​ለት፤ በግ​ዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገ​ስን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋራ ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት፤ በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ይሁን እንጂ ዮሴፍ እዚያ እስር ቤት ባለበት ጊዜ ሁሉ፥ ጌታ ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ቸርነቱንም አበዛለት፥ በወህኒ አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሆኖ ዘላቂ ፍቅሩን አሳየው፤ በእስር ቤቱ አዛዥ ዘንድ ባለሟልነትን እንዲያገኝ አደረገው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ ምሕረትንም አበዛለት

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 39:21
23 Referencias Cruzadas  

በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ፊት ለዚህ ሕዝብ ሞገ​ስን እሰ​ጣ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ዱም ጊዜ ባዶ እጃ​ች​ሁን አት​ሄ​ዱም፤


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ቢሆን፥ ክፉ ስለ ማድረግ ሳይሆን በጎ ስለ ማድረግ መከራን ብትቀበሉ ይሻላችኋልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሕ​ዝቡ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ፊት ሞገ​ስን ሰጠ፤ እነ​ር​ሱም አዋ​ሱ​አ​ቸው። እነ​ር​ሱም ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በዘ​በ​ዙ​አ​ቸው።


በውኃ ውስጥ ባለ​ፍህ ጊዜ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ ወን​ዞ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​ህም፤ በእ​ሳ​ትም ውስጥ በሄ​ድህ ጊዜ አት​ቃ​ጠ​ልም፤ ነበ​ል​ባ​ሉም አይ​ፈ​ጅ​ህም።


በኮ​ሬ​ብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተ​ሠራ ምስ​ልም ሰገዱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ፊት ለሕ​ዝቡ ሞገ​ስን ሰጠ፤ አዋ​ሱ​አ​ቸ​ውም፤ ይህ ሙሴም በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንና በፈ​ር​ዖን፥ በሹ​ሞ​ቹም ፊት እጅግ የከ​በረ ሰው ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዮ​ሴፍ ጋር ነበር፤ ሥራ​ውም የተ​ከ​ና​ወ​ነ​ለት ሰው ሆነ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊው ጌታ​ውም ቤት ተሾመ።


በዚያ ዘመን አቤ​ሜ​ሌክ፥ ሚዜው አኮ​ዘ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ፋኮል ወደ አብ​ር​ሃም ሄደው አሉት፥ “በም​ታ​ደ​ር​ገው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤


ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ።


በእ​ስር ቤት ውስ​ጥም ዮሴፍ ታስሮ በነ​በ​ረ​በት የግ​ዞት ስፍራ አጋ​ዛ​ቸው።


ነገር ግን በወ​ደ​ደን በእ​ርሱ ሁሉን ድል እን​ነ​ሣ​ለን።


ድን​ቅ​ንም በካም ምድር፥ ግሩም ነገ​ር​ንም በኤ​ር​ትራ ባሕር ያደ​ረ​ገ​ውን።


ጌታ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዮ​ሴፍ ጋር እን​ዳለ፥ እርሱ የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ እን​ዲ​ያ​ከ​ና​ው​ን​ለት አየ።


ዮሴ​ፍም በጌ​ታው ፊት ሞገ​ስን አገኘ፤ እር​ሱ​ንም ደስ ያሰ​ኘው ነበር፤ በቤ​ቱም ላይ ሾመው፤ ያለ​ው​ንም ሁሉ በእጁ ሰጠው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios