ዘፀአት 11:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዱ ከወዳጁ፥ ሴቲቱም ከወዳጅዋ የብርና የወርቅ ዕቃ፥ ልብስም ይዋሱ ዘንድ በሕዝቡ ጆሮ በስውር ተናገር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእስራኤል ሕዝብ፣ ለወንዶቹም ሆነ ለሴቶቹ የብርና የወርቅ ዕቃዎች ከየጎረቤቶቻቸው ስጡን ብለው እንዲወስዱ ንገራቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንዱ ከጎረቤቱ ሴቲቱም ከጎረቤቷ የብር ዕቃና የወርቅ ዕቃ እንዲጠይቁ በሕዝቡ ጆሮ ተናገር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁንም የእስራኤል ሕዝብ ወንዶቹም ሴቶቹም ጐረቤቶቻቸውን ሁሉ የወርቅና የብር ጌጣጌጥ እንዲሰጡአቸው ይጠይቁ ዘንድ ንገራቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንዱ ከወዳጁ ሴቲቱም ከወዳጅዋ የብርና የወርቅ ዕቃ ይሹ ዘንድ በሕዝቡ ጆሮ ተናገር አለው።” |
ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤቷ፥ በቤቷም ካለችው ሴት የብር ዕቃ፥ የወርቅ ዕቃ፥ ልብስም ትዋሳለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይም ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።”
ወንዶችና ሴቶችም ልባቸው እንደ ፈቀደ ማርዳዎችን፥ ሎቲዎችንም፥ ቀለበቶችንም፥ ድሪዎችንም፥ የወርቅ ጌጦችንም ሁሉ አመጡ፤ ሰዎችም ሁሉ የወርቅ ስጦታ ለእግዚአብሔር አቀረቡ።