La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 10:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ወደ ፈር​ዖን ጠሩ​አ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሂዱ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄ​ዱት እነ​ማን ናቸው?”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን እንዲመጡ ተደረገ፤ “ሂዱ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ነገር ግን መሄድ የሚገባቸው የትኞቹ ናቸው?” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴንና አሮንን ወደ ፈርዖን አመጡአቸው፦ “ሂዱ፥ ጌታ አምላካችሁን አገልግሉ፥ ነገር ግን የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አላቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ሙሴና አሮን ተጠርተው ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ንጉሡም “ሄዳችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁን ማገልገል ትችላላችሁ፤ ነገር ግን መሄድ የሚገባቸው የትኞቹ ናቸው?” አላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን መልሶ አስመጣቸው፤ ሂዱ፤ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ነገር ግን የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አላቸው።

Ver Capítulo



ዘፀአት 10:8
6 Referencias Cruzadas  

ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን በፍ​ጥ​ነት ጠራ፥ “በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ በእ​ና​ን​ተም ላይ በደ​ልሁ፤


ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ፤ ነገር ግን በጎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ብቻ ተዉ፤ ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶ​ቻ​ችሁ ግን ከእ​ና​ንተ ጋር ይሂዱ” አላ​ቸው።


ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን በሌ​ሊት ጠርቶ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተነሡ፤ ከሕ​ዝቤ መካ​ከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እን​ዳ​ላ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ል​ኩት፤


ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ በዚ​ያች ምድር ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ሠዉ” አላ​ቸው።


ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹን ከእኔ፥ ከሕ​ዝ​ቤም እን​ዲ​ያ​ርቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝ​ቡን እለ​ቅ​ቃ​ለሁ” አላ​ቸው።


እን​ግ​ዲህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ የአ​ም​ላክ ነጐ​ድ​ጓድ፥ በረ​ዶ​ውም፥ እሳ​ቱም ጸጥ ይላል፤ እኔም እለ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከዚህ አት​ቀ​መ​ጡም” አላ​ቸው።