Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 10:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለዚህ ሙሴና አሮን ተጠርተው ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ንጉሡም “ሄዳችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁን ማገልገል ትችላላችሁ፤ ነገር ግን መሄድ የሚገባቸው የትኞቹ ናቸው?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን እንዲመጡ ተደረገ፤ “ሂዱ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ነገር ግን መሄድ የሚገባቸው የትኞቹ ናቸው?” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሙሴንና አሮንን ወደ ፈርዖን አመጡአቸው፦ “ሂዱ፥ ጌታ አምላካችሁን አገልግሉ፥ ነገር ግን የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ወደ ፈር​ዖን ጠሩ​አ​ቸው፤ ፈር​ዖ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሂዱ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ልኩ፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄ​ዱት እነ​ማን ናቸው?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን መልሶ አስመጣቸው፤ ሂዱ፤ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ነገር ግን የሚሄዱት እነማን ናቸው?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 10:8
6 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “አምላካችሁን እግዚአብሔርንና እናንተን በድያለሁ፤


ንጉሡም ሙሴን ጠርቶ “ሄዳችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ሴቶቻችሁና ልጆቻችሁም ከእናንተ ጋር መሄድ ይችላሉ፤ ነገር ግን በጎቻችሁና ፍየሎቻችሁ የቀንድ ከብቶቻችሁም እዚህ መቅረት ይኖርባቸዋል።”


በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተና እስራኤላውያን ወገኖቻችሁ ሁሉ ከዚህ ውጡ! አገሬን ለቃችሁ ሂዱ! በጠየቃችሁትም መሠረት ለእግዚአብሔር ስገዱ!


ከዚህ በኋላ ንጉሡ ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ሄዳችሁ በዚህች አገር ውስጥ ለአምላካችሁ መሥዋዕት አቅርቡ” አላቸው።


ንጉሡም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ጓጒንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ዘንድ እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ ሕዝባችሁን እለቃለሁ” አላቸው።


በረዶውና ነጐድጓዱ እጅግ ስለ በዛብን ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልን፤ በእርግጥ እለቃችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እዚህ የምትቈዩበት ጊዜ አይኖርም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos