ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ አሉትም፥ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ማፈርን እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
ዘፀአት 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤን ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ፥ ነገ በዚህ ጊዜ በተራራዎችህ ሁሉ ላይ አንበጣን አመጣለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዳይሄዱ ብትከለክላቸው ነገ በአገርህ ላይ አንበጣዎችን አመጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቤን ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ እኔ ነገ በአገርህ አንበጣዎችን አመጣለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእምቢተኛነትህ ብትጸና ግን እነሆ፥ በነገው ቀን የአንበጣ መንጋ በአገርህ ላይ እንዲመጣ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቤን ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ ነገ በአገርህ አንበጣዎችን አመጣለሁ፤ |
ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ አሉትም፥ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ማፈርን እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
የምድሩንም ፊት ይሸፍናል፤ ምድሩን ለማየት አይቻልም፤ ከበረዶውም ተርፎ በምድር ላይ የቀረላችሁን ትርፍ ሁሉ ይበላል፤ ያደገላችሁንም የእርሻውን ዛፍ ሁሉ ይበላል፤
ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ልትለቅቃቸው ባትፈቅድ፤ እኔ የበኵር ልጅህን እንደምገድል ዕወቅ።”
ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲህ አሉት፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል ያደርግልኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።’ ”
እነሆ፥ ከተመሠረተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግብፅ ሆኖ የማያውቅ እጅግ ታላቅ በረዶ ነገ በዚህ ጊዜ አዘንባለሁ።
እግዚአብሔርም፥ “ነገ እግዚአብሔር ይህን ነገር በምድር ላይ ያደርጋል ብሎ ጊዜን ወሰነ።” እግዚአብሔርም ያን ነገር በነጋው አደረገ፤